በባህር ዳር ቀበሌ 11 ወጣቶችና በፖሊሶች መካከል ግጭት ተፈጠረ * አባላቱ በገፍ እየከዱት በሚገኘው አየር ኀይል አለመተማመኑ ስር ሰዷል

Photo File

አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 አባይ ማዶ ወጣቶች አንድ አካባቢ ላይ ተሰባስበው በመጫወት ላይ እያሉ ፖሊሶች ድንገት መጥተው “ለምን አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ቆማችሁ?” በማለት አምባጓሮ በመፍጠራቸው ነበር ግጭቱ የተነሳው፡፡ ፖሊሶቹ ወጣቶችን ከቆሙበት በኃይል አባረው ወደየቤታቸው ለማስገባት ሲሞክሩ ወጣቶቹ በፖሊስ ላይ የአጸፋ እርምጃ በመውሰዳቸው አንድ ፖሊስ ለከፋ ጉዳት እንደተዳረገ ታውቋል፡፡ የህወሓት አገዛዝ ለስልጣኑ የሚያሰጋውን የህብረተሰብ ክፍል እየመረጠ ትጥቅ ማስፈታቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አምባገነናዊ ስርአት የግብአተ መሬት ጊዜውን በጥቂቱም ቢሆን ያራዝምልኛል ብሎ ከነደፋቸው እቅዶች መካከል አንዱ የሆነውን ህዝቡን ትጥቅ የማስፈታት ተግባር በታች አርማጭሆ ገበሬዎች ላይ በተለየ ሁኔታ በግፍ የሚያስታጥቀው የህብረተሰብ ክፍል ያለው ዘረኛው የህወሓት ቡድን በአማርኛ ተናጋሪው ገበሬ ላይ አሁን እየፈፀመ የሚገኘው የትጥቅ ገፈፋ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ሲያደርገው የቆየው መሆኑ ይታወቃል፡፡ አባላቱ በገፍ እየከዱት በሚገኘው አየር ኀይል ውስጥ ተፈጥሮ የቆየው አለመተማመን ስር ሰዶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ታወቀ፡፡ ለሰላም ማስከበር ተልኮ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊሄዱ የተመለመሉት የአየር ሀይል አባላት የደቡብ ሱዳን ጉዞ ተሰርዞ ወደ ሱማሊያ እንደሚሄዱ ስለተነገራቸውና በግምገማ በመወጠራቸው ምክንያት በርካታ አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖች እና ሌሎች የተለያዩ ክፍሎች ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በመክዳት ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑም በአየር ሀይል ውስጥ አለመተማመኑ ገደቡን አልፎ አብራሪዎች ለልምምድ በሚያበሩት አውሮፕላን ውስጥ የህወሓት አባላት ከጎን እንዲቀመጡ እየተደረገነው፡፡ በተጨማሪም አብራሪዎች ነዳጅ በሚሞሉበት ጊዜ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡
Posted By/Lemlem Kebede
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s