ፌደራል ፖሊስ ባራክ ኦባማ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተዘጋጅተው ነበር ያላቸውን አሰረ * በክሱ ውስጥ ጋዜጠኛ ይገኛል

Habtamu

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ሰርግና ምላሽ በኢትዮጵያ ከወዲሁ የተወሰኑ እስረኞችና በመፍታትና ብዛት ያላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን በማሰር ወደ ቀኑ እየገሰገሰ ይገኛል፡፡የሰማያዊና የቀድሞው አንደነት አመራሮችና አባላት ኦባማ ወደ አገራችን ሲመጡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እያሴራችሁ እንደሆነ ደርሰንበታል በማለት ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ባሳለፍነው ሐሙስ የሞያ አጋሮቹ መፈተታት የፈጠረበትን ደስታ አጣጥሞ ሳይጨርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ምናለ ከአምስት ቀናት የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ዝግ ችሎት ተሰይሞ በፖሊስ የ15 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተጠይቆበት ያቀረበው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበት ወደ እስር ቤት እንዲመለስ መደረጉ አይዘነጋም፡፡ የአንድ ሳምንት የህትመት ብርሃን ካየች በኋላ በስርዓቱ ስልታዊ አፈና ዕድሜዋ እንዲቀጭ የተደረገችውን ‹‹ቀዳሚ ገጽ››ጋዜጣ በስራ አስኪያጅነት የመራት ሐብታሙ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ››ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ሰርቷል፡፡አስቂኙ የእስር ክስ እንደቀረበበት ከመደመጡ አስቀድሞም ‹‹ለጥያቄ እንፈልግሃለን››ባሉት ደህንነቶች ተይዞ ቃሉን እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ መለቀቁ ይታወሳል፡፡ የሞያ አጋራቸው ከታሰረበት ዕለት አንስቶ የእስሩን ምክንያት ለማወቅ ሲታትሩ የነበሩት ጋዜጠኞች ኤልያስ ገብሩና ኢዮኤል ፍስሐ ለማመን የከበዳቸውን የፈጠራ ክስ ከራሱ ከሐብታሙ አንደበት አዳምጠው ተመልሰዋል፡፡ሐብታሙ ‹‹የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባል በመሆን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ጥቃት ለመፈጸም ስትንቀሳቀስ ነበር››መባሉን ነግሯቸዋል፡፡ የፈጠራ ክስ በገዛ ዜጎቹ ላይ በማቅረብና በማስወንጀል የዳበረ ሪከርድ ያለው የፌደራሉ ፖሊስ ጋዜጠኛውን ለሽብር ድርጊቱ ተዘጋጅተው ያዝኳቸው ካላቸው 44 ተጠርጣሪዎች ጋር በአንድ መዝገብ ማቅረቡም ነገሩን አሳዛኝም አሳፋሪም ያደርገዋል፡፡ከተጠርጣሪዎቹም መካከልም የሶሪያና ሶማሌያዊ ዜግነት ያላቸው ስዊዲናዊያን እንደሚገኙበት ኦባማ ላይ ጥቃት ለማድረስ አሴረሃል የተባለው ሐብታሙ ተናግሯል፡፡

Posted By- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s