ሼህ አላሙዲን እና አየር ኃይል የት ይተዋወቃሉ?

 

የአንዳንድ አርቲስቶች ከሀገር እየወጡ መቅረት እንዲሁም ግፋ ሲል ስርዓቱን በግልጽ መቃወም የሚያመጣው ተፅዕኖ የተረዱ የሚመስሉት የስርዓቱ ደጋፊዎች እና መሪዎች ለሌሎቹም መማማሪ እንዲሆን በሚል ይመስላል ሼህ መሀመድ አላሙዲን ረብጣ ገንዘብ አፍ በማዘጋት ላይ ናቸው፡፡ የኚህ ሰውየ ገንዘብ በአብዛኛው የሚወጣው ሰውን ለመግዛት ወይም በፖለቲካ አቋሙ ማሳመን ያልተቻለውን በገንዘብ ሀይል ማሳመኛነት ብቻ ይመስላል፡፡ ከዚህ ቀደም የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ውድድር አመራሮች ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር እንደተፈታች እሷን በመጋበዝ ያሳዩት ድፍረት እና የድርጅቱ ጥንካሬ እያደገ መሄድ ያልተመቻቸው የስርዓቱ ሰዎች የኚህን ሰውዬ ረብጣ ገንዘብ በመጠቀም ጥቂቶችን በመግዛት ድርጅቱን የማዳከም ስራ ሞክረው እንደነበረ አይዘነጋም፡፡
እነሆ የዛሬው ባለእጣ ደግሞ የቀድሞ የአየር ሀይል ማህበር ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከአመታት በፊት የቀድሞ አየር ኋይል ቤተሰብ አባላት በዲሲ ተሰባስበው ታላላቆቻቸውን እና የሀገሪቱን ጀግኖች ሲያወድሱ ላየ በስርዓቱ መሪዎች ጥርስ ውስጥ እንደገቡ ለመገመት ዛሬን መጠበቅ አያስፈልግም፡፡ ዛሬ እነዛ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲዘምሩ ያየናቸው ጀግኖች ሁለት ልብ ሆነው ሲወዛገቡ እያነበብን ነው፡፡ ሲጀምር ሼኽ አላሙዲን እና ሸራተን በየትኛው መስፈርት ነው የአየር ሀይልን ታሪክ መጽሐፍ አሳታሚ እና አስመራቂ የሚሆኑት? እንደምንሰማው ለውዝግቡ መነሻ በአየር ኀይል አባላት ስም ተጻፈ የተባለው መጽሐፍ ነው፡፡ ይሄን መጽሐፍ ህትመት እና ምርቃት ስፖንሰር ያደረጉት ደሞ አላሙዲን ናቸው፡፡ ሌላኛው መራቂ ደሞ ቀድሞ የአየር ሀይል አባል የነበሩት መ/ቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ መቶ አለቃ ግርማ በዓየር ኃይል ላይ የሞት ፍርድ ያጸደቁ ሰው ናቸው፡፡ ይሄ ሁሉ ግርግር ለዓየር ሀይል አባላት ክብር እንዳልሆነ በደንብ ያሳብቃል፡፡ ይልቅ በዓየር ሀይል አባላት መካከል ያለውን ቤተሰባዊ ግንኙነት መበጠስ ይመስላል፡፡
ከ1921 ዓ.ም እስከ 1991 ኢትዮጵያ – ኤርትሪያ ጦርነት በርካቶ ስለሀራቸው ብቻ ሲሉ ህይወታቸውን የሰጡበት፣ የታሰሩበት፣ የተገረፉበት፣ አካላቸውን ያጎደሉበት ተቋም አየር ኃይል ዛሬ ያለበትን ደረጃ እና ለነዚህ ቤተሰቦቹ የሰጠው እውቅና ለመረዳት እነዛ በሶማሊያ ጦርነት ወቅት እንደተረት የምንሰማቸው ጀግኖች የት እናዳሉ እንዴት እንደሚኖሩ አንዱን የዓየር ኃይል ቤተሰብ ቀረብ ብትሉት ይነግራችኋል፡፡ ታዲያ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እንደዛ በየመንገዱ የወደቀውን ቤተሰቡን ማንሳት ያልቻለ ሸራተን ተሰብስቦ በውስኪ የሚራጨው፡፡ መልሱ አንድ ይመስላል …
“አንድ ነገር ሲያምር ያየሁት እንደሆን
እሱን ካላጠፋሁ ከቶ ምንም ቢሆን
እንቅልፍም አይወስደኝ…”
ብዙዎችን ያስደመመው የዓየር ኋይል ቤተሰብን የመከፋፈል አጀንዳ ይመስላል፡፡ ይሄንን ለመረዳት የተለየ እውቀት አያስፈልግም፡፡ የዓየር ኋይል ቤተሰቦች በዚህ መጽሐፍ ካገኛችሁት እያጣችሁ ያላችሁት የበዛ ይመስላል፡፡ እናም እንደኔ አይነቱ የእናንተን አኩሪ ታሪክ እንደተረት ተረት ሲሰማ ላደገ ትውልድ እና ለነዛ የሚገባቸውን ክብር ሳያገኙ ለተሰው ጀግኖች ስትሉ፡፡ የዚህ መጽሐፍ ጉዳይ ትታችሁ ቤተሰባችሁ በመሰብሰብ ላይ ብታተኩሩ የሚሻል ይመስለኛል፡፡

Posted By-Lemlem Kebede

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s