ሰበር ዜና አርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በወያኔ ሰራዊት የኃይል ጥቃት ሰነዘረ፥

 

 

ሰበር ዜና
================================================
ትናንት ሀሙስ ዕለት ሰኔ 25 2007 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በትግራይ ክልል ቀፍታ መሲል፣ ሆርጃሞ እና ማይሰገል ላይ ህወሓት ከሚቆጣጠረው የ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ጋር ባደረገው ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ጦርት ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ተጋዮች በትግራይ ቀፍታ መሲልና ሆርጃሞ ላይ መሽጎ ያገኙትን ከሶስት ክፍሎች ማለትም ከ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ከፌደራል ፖሊስና ከልዩ ኃይል የተውጣጣና እስከ አፍንጫው የታጣቀ ቁጥር ስፍር የሌለው ጦር ከቀኑ ሰባትሰዓት እስከ አስር ሰዓት ለተከታታይ ሦስት ሰዓታት በጥይት ቆልተውታል፡፡

በተጨማሪም እዚያው ትግራይ ውስጥ ማይሰገል በተባለው ቦታ ምሽት ከአስራ ሁለት ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት በተደረገው ፍልሚያ በጠላት ጦር ሰራዊት ላይ ከፍተኛ እልቂት ደርሷል፡፡
ትግራይ ውስጥ በሚገኙ በሦስቱ ቦታዎች በተደረው አራት ሰዓታትን የፈጀ መራራ ውጊያ ከተለያዩ ሶስት ክፍሎች የተደራጀው የጠላት ጦር በአርበኞች ግንቦት ሰባት የነፃነት ፋኖዎች ፈርጣማ ክንድ ክፉኛ ተደቁሶ የተበታተነ ሲሆን በትንሹ ከ50 በላይ ወታደሮች ሲሞቱ ከ60 በላይ ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ ህወሓት በሚቆጣጠረው ሰራዊት ላይ የደረሰው ጉዳት አሁን ገና በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ውሎ አድሮ ትክክለኛው መረጃ ሲገኝ የሞቱትና የቆሰሉት ወታደሮቹ ቁጥር አሁን ከተገለፀው ከሁለትና ሦስት እጥፍ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይገመታል፡፡

ስለዚህም በአሁኑ ሰዓት አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት አውጇል በሚል ከሁመራ-ዳንሻ፣ ከሁመራ-ሽሬ እና እንዲሁም በተጨማሪ ከሁመራ-ጎንደር የሚገኙት አውራ ጎዳናዎች ጥርቅም ብለው በጦር ሰራዊት ተዘግተው ምንም አይነት የመኪና እንቅስቃሴ የለም፡፡

እስከ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የኖረው ህወሓትን በጠብመንጃ የማስወገዱ ጦርነት ፍልሚያ አብሳሪ የሆነው ፊሽካ በአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ እነሆ ተነፍቷል፡፡ በመሆኑም ነፃነት ፈላጊ የሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ/ወጣት ሁሉ በያለበት ትጥቅ ያለው ትጥቁን አንስቶ፣ ድንጋይና ዱላ የጨበጠም በእጁ በሚገኝ ማናቸውም መሳሪያ የዘረኛውን አገዛዝ የህወሓትን ቡድን ራስ ራሱን በመቀጥቀጥ በረሃ ወርደው በመፋለም ውድ ህይወታቸውን እየከፈሉ ከሚገኙት ልጆቹ፣ ወንድሞቹ እና እህቶቹ የሆኑ አርበኛ ታጋዮች ጎን አንዲሰለፍ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ፍልሚያው አሁንም እንደ ቀጠለ ነው!

ዛሬ ረፋድ 4፡30 ላይ /አርብ ሰኔ 26 2007 ዓ.ም/ በትግራይ ክልል በዋል /በተለምዶ መሀመድ ሸሪፍ/ የእርሻ ክምፕ አካባቢ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህወሓት ከሚቆጣጠረው ጦር ሰራዊት ጋር ከባድ ውጊያ አድርጓል፡፡
ህወሓት በሚመራው ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በትንሹ 30 ወታደሮች ሲገደሉ 20 በፅኑ ቆስለዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ቁጥሩን ከሦስት እጥፍ በላይ አሳድገው እየገለፁት ይገኛሉ፡፡
በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህወሓት በሚቆጣጠረው የመከላከያ ኃይል ላይ ባሳረፈው ጠንካራ ምት አንድ የመቶ አለቅነት ማዕረግ ያለው ወታደራዊ አዛዥ እና ካህሳይ ነጋሽ የተባለው የባህከር ሚሊሻ ኮማንደር ተገድለዋል፡፡
ጦርነቱ እየተካሄደባቸው የሚገኝባቸው አካባቢዎች ህዝብ ሞራሉ ተነሳስቶ ከአርበኛ ታጋዮች ጎን እየተሰለፈ የሚገኝ ሲሆን በህወሓት መንደር ደግሞ ታላቅ ሽብር ነግሷል፡፡
በህወሓት ሰራዊት ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የሞቱት እና የቆሰሉት ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ የሚገኝ ስለሆነ መረጃውን አጠናቅረን እንደጨረስን ወደፊት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃንና በዚሁ የሶሻል ሚዲያ የምናሳውቅ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን፡፡

Source/Aseged Tamene

Posted By/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s