ጋዜጠኛ ሚካኤል ዲኖ የሚያስተዳድራቸው ደካማ እናቱንና ተሰናብቶ፣ የሚወዳትን አገሩን ጥሎ ተሰደደ

Ethiopian journalist in exile Mikael Dino

ሚካኤል ዲኖ ይባላል። የአዲስ አበባ ልጅ ነው። ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ጋዜጦች እና የሬድዬ ፕሮግራሞች ፅሁፎችን በማቅረብ የጋዜጠኝነት ሙያን እንደተቀላቀለ መረጃዎች ያሳያሉ።

በ2002ዓ.ም በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በምትዘጋጀው ፍትሕ ጋዜጣ ላይ በሪፓርተርነት እና በዓምደኝነት እየሰራ፣ ጋዜጣዋ የተደበቀውን የመለስ ዜናዊ ሞት በማተሟ እስከተዘጋችበት ግዜ ድረስ አገልግሏል።

ከዚህ በኃላ በአስገራሚ ሁኔታ… “ልዕልና”፣ “አዲስ ታይምስ”፣ በመጨረሻም ፋክት መፅሄት ድረስ አንዱ ሲዘጋ ሌላ በመክፈት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ የሪፓርተርነትን ሚና በዋነኝነት፣ የአምደኝነትን ደግሞ በመጋቢነት እየተወጣ፤ በመጨረሻ ድርጅቱ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ተወርሶ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሶስት አመት የግፍ እስር እስኪበየንበት ድረስ ከሙያ አጋሮቹ ጋር ግዴታውን ሲወጣ ቆይቷል።

በፋክት መፅሄት ሪፓርተርነቱ የምርመራ ጋዜጠኝነትን በመጠቀም፣ በአፋር ክልል “መንደር ማሰባሰብ” በሚል ሽፋን በአዋሽ ዳርቻ የሚገኙትን ነዋሪዎች በማፈናቀል በርካሽ ዋጋ ለህንድ ካምፓኒዎች መሰጠቱን፣ የክልሉን በመሰረተ ልማት እጅግ ወደኃላ መቅረት እንዲሁም የተንሰራፋውን ሙስና አስመልክቶ ለዘጠኝ ሳምንታት በተከታታይ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ በመጀመሩ፣ በራሱ እና በቤተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና ቢደርስበትም እስከመፅሄቷ መዘጋት ድረስ ትረካውን አላቆመም። በ2006ዓ.ም “ሕዝብ እና ነፃነት” የተሰኘውን ጠንካራ ሂስ ያዘለ መፅሀፉ መታተምን ተከትሎ፣ የደህንነት ሀይሎች ክትትል እና የማእከላዊ ማስጠንቀቂያን እያስተናገደ ቆይቷል።

በመጨረሻም የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ (አንድነት) ፓርቲ ልሳን የነበረችውን ፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣን በምክትል ዋና አዘጋጅነት በማዘጋጀት፤ የፓርቲው ህልውና እስካከተመበት ግዜ ድረስ አገልግሏል።

ጋዜጠኛው እንዲህ ባለው ፈታኝ አውድ ውስጥ በፅናት ሲታገል ቢቆይም፣ የደህንነቶቹን ጫና መቁዋቁዋም ስላልቻለ እና በተለመደው የሽብርተኝነት ስያሜ ሊከስሱት እንደሆነ መረጃ በማግኘቱ፣ የሚያስተዳድራቸው ደካማ እናቱንና ተሰናብቶ የሚወዳትን አገሩን ጥሎ ለመሰደድ በቅቷል።

Source/ethiopiareview.com

Posted By/ Lemlem Kebede

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s