የ40/60 ቤቶች ዕጣ ድልድል ትኩረት ይሰጠው

መንግሥት ብዛታቸው 1,292 የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤቶችን ለተመዝጋቢዎች በቅርቡ እንደሚያስተላለፍ ማስታወቁ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

በዚህ ፕሮግራም የመጀመርያው የቤት ማስተላለፍ ሥነ ሥርዓት ሲካሔድ የቤት ባለቤት መሆናቸው ከሚበሰርላቸው በተጨማሪ፣ ለቀሪዎቹ ቆጣቢዎች ተስፋ ሰጪ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡

የቤት ባለቤት ዕድለኛ የሚኮንበትና ዕድሉ የሚሰጥበት አካሄድ ግን በጥልቀት ታስቦበት ፍትኃዊ፣ የማያሻማና ተገቢ መመዘኛ ሊቀመጥለት ይገባል፡፡ የቤት ባለቤትነት ዕድል ሊሰጥ የሚገባው ተመዝጋቢው የቆጠበበትን ጊዜና የተቆጠበውን መጠን መሠረት አድርጎ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህን መመዘኛ ተገቢ የሚያደርገው ምክንያት ምንድን ነው ከተባለም፣ አንድ ተመዝጋቢ ቤት ለማግኘት እጁ ላይ ያለውን ገንዘብም ሆነ፣ ተብድሮ ወይም ያለውን ጥሪት ሸጦ አለያም ሌሎች ማናቸውንም ምንጮች ተጠቅሞ ገንዘቡን የሚከፍለው፣ ቤቱን በቅድሚያ ለማግኘት ካለው ፍላጎትና ጉጉት አንፃር መሆኑ ከግንዛቤ እንዲገባ መግባት አለበት፡፡ 

አንድ ተመዝጋቢ የቤቱን ዋጋ መቶ ከመቶ ምዝገባው በተጀመረ ዕለት ሊከፍል ይችላል፡፡ ሆኖም ገንዘቡን ከአሥር ቀናት በኋላ አቆይቶ ከተመዘገብም፣ በአሥር ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ሊያስገኝለት የሚችለውን ማንኛውንም ጥቅም በመተውና ቤቱን ለማግኘት መስዋዕትነት በመክፈል ያደረገው ነው፡፡ ይህ ስሌት በገንዘቡ የሚነግድን ግለሰብ በማሰብ ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ ገንዘብ ከጊዜ ጋር ያለውን ዋጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊታይ የሚገባው መሆኑን ለማመላከት የቀረበ ነው፡፡ ገንዘቡ ቀድሞ በባንክ መግባቱ ደግሞ የቤቶቹን ግንባታለሚያከናውነው አካል የገንዘብ አቅሙን የሚያሳድግና ግንባታዎችን ለማፋጠን የሚረዳ ከመሆኑም በላይ፣ ቀድመው ብዙ የቆጠቡ ተመዝጋቢዎች ቀድመው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያደርግ አሠራር በግልጽ ቢዘረጋ፣ ሌሎችም በተቻላቸው መጠን ቅድሚያና ትኩረት ሰጥተው በርከት ያለ ገንዘብ በቶሎ እንዲቆጥቡ የሚያበረታታ አካሄድ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ሌላው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የቁጠባ መጠንና የቁጠባ ጊዜ ሁለቱም በተጠና የመመዘኛ መስፈረት በጥንቃቄ የሚታዩበትን አሠራር መቀየስ ነው፡፡ አንድ ሰው መቶ ከመቶ ከፍሏል ወይ? ብቻ ሳይሆን መቼ ነው የከፈለው? የሚለውም ወሳኝነት አለው፡፡ ከአጠቃላይ የቤቱ ዋጋ 80 ከመቶውን  ምዝገባ በተጀመረ ጊዜ ያስገባና ቀሪውን 20 ከመቶ ከዓመት በኋላ ያስገባ ተመዝጋቢ፣ ዝቅተኛውን የወር ክፍያ ብቻ ሲከፍል ከርሞ በአንድ ጊዜ ምዝገባ ከተጀመረ ከዘጠኝ ወር በኋላ መቶ ከመቶ ክፍያ ላይ ቢደርስ፣ 80 ከመቶውን በምዝገባ ወቅት ከከፈለው አኳያ ቅድሚያ ሊሰጠው አይገባም፡፡ በመሆኑም ተመዝጋቢው የቆጠበውን የገንዘብ መጠንና የቆጠበባቸውን ጊዜዎች ከግምት በማስገባት የቤት ባለቤት ለመሆን ቅድሚያ የሚሰጥበትን ስሌት መቀመር የሚገባ ይመስለኛል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ40/60 ቤቶች ምዝገባ ከማካሄዱ በፊት ይፋ ባደረገው ፕሮግራሙ አጠቃላይ ይዘት ውስጥ፣ የቤቱ ድልድል ቅድም ተከተል በደንበኞች የቁጠባ መጠን ልክ፣ በምዝገባ ጊዜና በዕጣ እንደሚሆን በግልጽ አስቀምጦ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት እኩል መቶ ከመቶ የከፈሉ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባው የተመዘገቡበትን ጊዜ መሠረት አድርጎ መሆን አለበት ማለት ነው፡፡  ለምሳሌ በመጀመርያ ቀን የተመዘገቡና መቶ ከመቶ የከፈሉ በሁለተኛው ቀን ከተመዘገቡና መቶ በመቶ ከከፈሉት ይልቅ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የከፈሉበት ቀን ተመሳሳይ ከሆነም  የከፈሉበት ሰዓት ጭምር እንደመመዘኛ ተውስዶ ፍትኃዊ አሠራር ሊዘረጋ ይገባል፡፡ አለበለዚያ በእኩል መጠን የቆጠበውን ሁሉ በአንድ ዓይን በማየት፣ በዕጣ ባለዕድሎችን ለመለየት የሚደረግ አካሄድ የሚተገበር ከሆነ፣  ቁጠባን አያበረታታም፡፡ ለቁጠባም ቅድሚያ የሰጡትንና የሚሰጡትን ያስቀይማል፡፡ በእኔ አመለካከት፣ ለሴቶችና ለመንግሥት ሠራተኞች የሚሰጠው ኮታ እንደተጠበቀ ሆኖ በ40/60 ፕርግራም ቤቶችን  በዕጣ  የማስተላለፍ  ሒደት ላይ መሠረታዊ የአሠራር ግድፈት የሚፈጥርና ኢፍትኃዊ አካሔድ ስለሚሆን፣ ቤቱ የሚተላለፈው የተመዝጋቢዎችን የቁጠባ መጠንና የምዝገባ ጊዜ ብቻ መሠረት ማድረግ መሆን ይገባዋል፡፡ 

ሌላው በመገናኛብዙኃን ከሰሞኑ ከሚሰሙ ወሬዎች መካከል በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሚደለደሉት የ40/60 ቤቶች ላይ፣ ቀድሞ ከተገመተው የቤቶቹ ዋጋ ላይ ጭማሪ እንደሚደረግ የሚያመለክተው ነው፡፡ ጭማሪው ይኖራል ከተባለ ግን ቀድሞ የቤቶቹ ዋጋ በተተመነበት ወቅት ሙሉ በሙሉ የቤቱ ዋጋ የተከፈለ ከሆነ፣ ወይም ቆጣቢው ቤቱን ከመረከቡ በፊት የቆጠበው የገንዘብ መጠንና ጊዜ ታይቶ የዋጋ ጭማሪው ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡ ቤቱን እስኪረከብ ድረስ ጥቂት ብቻ የቆጠበና ሙሉውን የቤት ዋጋ ግምት ወይም አብዛኛውን ቀድሞ ለከፈለ፣ አሁንም የዋጋ ጭማሪው ሥሌት ሲሠራ እንደ መመዘኛ ሊታይ ይገባል፡፡ ዋናው ነገር ግን፣ መንግሥት በወቅቱ ባለው የግንባታ ግምት ቀድሞ ገንዘቡን መቶ ከመቶ የወሰደ በመሆኑና ግንባታውንም ሲያካሂድበት ቆይቶ ከሁለት ዓመት በኋላ አሁን ቤቱን ሲያስረክብ ባለፉት ሁለት ዓመታት የጨመረውን ዋጋ በደፈናው መሠረት ያደረገ ጭማሪ እንዳያሰላ ቢታሰብበት፡፡

Source-zehabesha.com

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s