መራጭ አስመራጭ ተመራጭ የሆነው ኢሃዲግ የስሙላ ምርጫውን ኮሮጆውን በመሙላት አጠናቀቀ

ሳይጀመር የተጠናቀቀው፡ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት ውጤቱ የታወቀው፡ ቀኑ ሳይደርስ አሸናፊው የተረጋገጠለት፡ መራጩ፡ አስመራጩ፡ ተመራጩ፡ ዓለም ዓቀፉ ማህብረሰብም ሁሉም ቀድመው ውጤቱን ያወቁለት ምርጫ 1997–ምርጫ 2002– ምርጫ 2007። ትላንት የተካሄደው ምርጫ ወያኔ ኢህአዴግ ማናልብኝነቱን ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለዉን ንቀት ፣ አንዲሁም አይን ያወጣ ቀጣፊንቱን በአደባባይ ፀሐይ ሲያስመታዉ የዋለበት ዕለት ሆኖ አልፏል።
የትላንቱ ምርጫ በአብዛኛው በወከባ ተጀምሮ በወከባ የተጠናቀቀ፡ ኮሮጆዎች ሌሊቱን ሲሞሉ ያደሩበት፡ የተቃዋሚ ታዛቢዎች የተገፉበት፡ በሰራዊት የተጥለቀለቀ፡ እንደነበር ከየአቅጣጫው አየወጡ ያሉት መረጃዎች ያመለክታሉ።
ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ የወያኔ ኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑ የመገናኛ ብዙሃን (ለምስሌ አይጋ ፎረም)የአንዳንድ አከባቢዎችን ውጤቶች እየገለጹ ናቸው። በአዲስ አበባና በጎንደር ገዢው ስርዓት ሙሉ በሙሉ አሸንፏል እያሉ ናቸው። ዶክተር መረራ ጉዲናና ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን በተወዳደሩባቸው ቦታዎች በወያኔ ካድሬዎች ተሸንፈዋል ብሏል።

በተለያዩ የጎንደር አከባቢዎች መጠነ ሰፊ አፈናና አፈሳ እየተካሄደ ነው። በቀበሌ 18 ባህረ ሰላም ሆቴል ውስጥ ትላንት 4 ወጣቶች የመከላከያ ሰራዊት ትጥቅ በለበሱ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል። በደምቢያም 20 ኢትዮጵያውያን በፌደራል ፖሊስ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። ከመሃላቸው በ4ቱ ላይ በተፈጸመ ከፍተኛ ድብደባ ለህይወታቸው አስጊ በሆነ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።
ይህ በዚህ እንዳለ በምርጫው ግርግር ይፈጠራል በሚል የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መንግስት ባለስልጣናት ቤተሰቦቻቸውን ወደ ውጭ ሀገራት እየላኩ መሆናቸውን ኢሳት ሀግቦአል። በቦሌ በኩል እየተሸኙ ያሉት የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ አሜሪካና አውሮፓ የሚያመሩ እንደሆነም ተገልጿል። ባለስልጣናቱ ግን እንዳይወጡ በህወሀት ቁንጮ መሪዎች እንደታገዱም ከምንጮች መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

እስኪ ያሳያችሁ እንግዲህ ሌላዉን ትተን በጥቂቱ እንኩዋን ብንመለከት ከሶስት ዓመት በላይ ፍትህ ያጣዉ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ….የወያኔ ኢህአዴግ ቅጥ የለሽ አገዛዝ መቁአቁአም ከብዶአቸዉ አንጀራ ፍለጋ ከሀገር ተሰደዉ የበረሃ እራት የሆኑባቸዉ ቤተሰቦችና ወዳጆች፣ በሀገሩ ፍትህና የዜግነት ክብሩን በአደባባይ ተነፍጎ የሚኖረዉ ማህበረሰብ ፣ እኩል የሆነ የሰራ እደል ያለተፈጠረለት በኢህአዴግ አድሜ ላይ የሚገኝ ወጣት፣ በመብራትና ዉሃ አንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ እየተምዘገዘገ ሽቅብ የሚወጣዉ የኑሮ ዉድነት ያስመረረዉ ኢትዮጵዊ ድምፁን ለውያኔ እንደማይስጥ ይታወቃል፡፡ እንግዲህ ወያኔ ይህን በጣም ቀላል ሂሳብ ማስላት ተስኖት ወይም በማናለበኝነት ይህዉ 24ቱን ጨርሶ ሌላ የ5 ዓመት እድሜ ማራዘምያዉን ትላንት 100% ተወግቶ ጨረሰ፡፡ ከንግዲህ በሰላማዊ መንገድ ወያኔን ከስልጣን ማስወገድ ተስፋ የለሽና የሳት ዳር ጨዋታ ከሆነ ሰነባብቷል፤ ስለዚህም ሁለት አማራጮች ተሰተዉናል አንድ የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል የለዉጡን ሂደት ማፋጠን ሁለት በሳት መጫወት፡፡ እኔ አንደኛዉን መርጫለሁ እናንተስ????

Posted By/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s