ጋዜጠኛ ሊሊ መንገሻ በኢትዮዽያ ባለው የፕሬስ ነፃነት ጉዳይ ከባራክ ኦባማ ጋር ውይይት አደረጉ

ዋሽንግተን፥ በፕሬስ ነጻነት ላይ የሚደርሰው ጥቃት ተወገዘ።  የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ  በዓለም ዙሪያ በፕሬስ ነፃነት ላይ የሚቃጣውን ጥቃት አወገዙ። ፕሬዚዳንቱ  የፕሬስ ነጻነት «እጅግ ከታፈነባቸው»  ሃገራት የመጡ ያሏቸውን ሦስት ጋዜጠኞችን በኋይት ሐውስ ጠርተው  ያነጋገሩ ሲሆን፤ አንደኛዋ ጋዜኛ ከኢትዮጵያ መሆኗ ታውቋል። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ  በጽ/ቤታቸው ጠርተው ያነጋገሯቸው ጋዜጠኞች፦ ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ሊሊ መንገሻ፣ ሩስያዊቷ ፋቲማ  ትሊሶቫ  እና የቬትናሙ  ጦማሪ ዲዩ ካይ  ናቸው። ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ወቅት «ያለመታደል ሆኖ በዓለማችን በርካታ ቦታዎች እውነትን ለማጥፋት በሚፈልጉ አለያም ዜጎች የራሳቸውን ውሳኔ ራሳቸው እንዳይወስኑ በዜጎቻቸው ላይ እምነት የሌላቸው መንግሥታት ነፃው ፕሬስ ጥቃት እየተሰነዘረበት ነው»  ሲሉ ጥቃት አድራሾቹን አውግዘዋል። የኦባማ  ውግዘት የተከተለው  Freedom House  የተሰኘው ተቋም እና የሠብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅቶች በዩናይትድ ስቴትስ እና በቻይና ብሎም በመላው ዓለም የፕሬስ ነፃነት እጅግ እየተጣሰ ነው የሚል ነቀፌታ ካቀረቡ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያዊቷን ጨምሮ ሦስቱ ጋዜጠኞች  ባሉበት የጋዜጠኞችን ሚና ያወደሱት የዓለም የፕሬስ ቀን ከሚከበርበት ኹለት ቀናት ቀደም ብሎ ትናንት ነበር።

Posted By/Lemlem Kebede

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s