ብራስልስ፣ የአውሮጳ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ እና ትኩረቱ

European Union flag

የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች እና መራህያነ መንግሥት አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው የጀልባ ስደተኞች ጉዳይ ለመምከር ዛሬ በብራስልስ ቤልጅየም አስቸኳይ ጉባዔ  ጀመሩ። መሪዎቹ ስደተኞች ወደ አውሮጳ ለመግባት ሲሞክሩ በሜድትሬንያን ባህር የሚሰምጡበትን አደጋ ለማብቃት እና የሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎችን መረቦችን ለማፈራረስ ያስችላል በሚል የውጭ ጉዳይ እና የሀገር አስተዳደር ሚንስትሮቻቸው በሳምንቱ መጀመሪያ ያዘጋጁትን ባለ አስር ነጥብ እቅድ ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። በእቅዱ መሠረት ተጨማሪ ገንዘብ እና መርከቦች ለማሰማራት ታስቦዋል። ስደተኞች የመጀመሪያ መዳረሻ ያደረጉዋት የኢጣልያ ጠቅላይ ሚንስትር ማቴዎ ሬንሲ ከዛሬው ጉባዔ  ብዙ እንደሚጠብቁ በማመልከት ህብረቱ ስደተኞችን እልቂት በማስቆሙ ረገድ ወሳኝ ሚና ሊጫወት እንደሚገባው አሳስበዋል።

« ይህ የሰብዓዊ መብትን የሚመለከት ነው። እና በአሁኑ ጊዜ ኢጣልያ ቅድሚያ ትኩረት የምትሰጠው የአውሮጳ ህብረት ዳግም የፖለቲካ አስተዋፅዖ እንዲያደርግ ነው ብለን በድፍረት ልንናገር ይገባል። ነው። የአውሮጳ ህብረት የነፍስ አድን ጥረት ሊጠናከር ይገባዋል። »

የአውሮጳ ህብረት ማብቂያ ያልተገኘለትን የስደተኞች ሞት ለማብቃት ባስቸኳይ ርምጃ እንዲወስድ የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን ማሳሰባቸውን የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪች ትናንት አስታውቀዋል።

« ዋና ጸሐፊው ነገ በብራስልስ የህብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ከመካሄዱ በፊት ለአውሮጳ ህብረት የሚንስትሮች ምክር ቤት ፕሬዚደንት ዶናልድ ቱስክ ደብዳቤ ልከዋል። ዋና ጸሐፊው በዚሁ ደብዳቤ ላይ በሜድትሬንያን ባህር የስደተኞች ህይወት መጥፋት የቀጠለበት ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። የአውሮጳ ህብረት በባህሩ የሚከሰተውን ሰብዓዊ እልቂት ለማብቃት አጠቃላይ እና ቆራጥ የጋራ ርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል። ከዚህ በተጨማሪም ወደ ውጭ የሚሄዱትን ሰዎች እና ስደተኞችን ደህንነት መጠበቅ፣ ከለላ መስጠት እና ሰብዓዊ መብታቸውን ማስከበር የመፍትሔው ማዕከላይ ነጥብ መሆን እንደሚኖርበት አስታውቀዋል። »

የአውሮጳ ህብረት በተለይ በሊቢያ ይንቀሳቀሳሉ ያላቸውን የሕገ ወጦቹን ሰው አሸጋጋሪዎች መረቦችን ለማፈራረስ ወታደራዊ ርምጃ ሊወሰድ የሚችልበትን አማራጭም በማሰላሰል ላይ መሆኑን የዜና ምንጮች የህብረቱን ባለሥልጣናትን በመጥቀስ አስታውቀዋል። በዚሁ መሠረትም፣ በቅርቡ ይጀመራል በሚባለው የህብረቱ ወታደራዊ ርምጃ ከ600 የሚበልጡ የጀርመን ባህር ኃይል ወታደሮች ሊሳተፉ እንደሚችሉ ተገልጾዋል።   ይሁንና፣ ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘው የሊቢያ አመራር ውጭ ጉዳይ ሚንስትር መሀመድ አል ጊራኒ መንግሥታቸው ይህን ዓይነቱን ርምጃ በቸልታ እንደማይመለከተው አስጠንቅቀዋል። ይህ በዚህ እንዳለ፣ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናልም የአውሮጳ ህብረት መሪዎች ያፀድቁታል የሚባለውን ባለ 10 ነጥቡ የድርጊት መርሀግብር ከስደተኞች የሰብዓዊ መብት ይልቅ ለፀጥታ ጥበቃው እና ለፀረ ወንጀል ትግሉ ትኩረት የሰጠ ነው በሚል ነቅፎታል።

dw.de.com

Posted By/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s