አዲስ አበባ-የሐዘን ሠልፍና ግጭት

 

 

እራሱን እስላማዊ መንግሥት (IS) ብሎ የሚጠራዉ ቡድን ሊቢያ ዉስጥ የገደላቸዉን ኢትዮጵያዉያን ዛሬ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የአዲስ አባባ ነዋሪ በሠልፍ አሰባቸዉ።የአዲስ አበባን መስቀል አደባባይ ያጥለቀለቀዉ ሕዝብ ግድያዉን አዉግዞ፤ ሟቾችን  ሻማ በማብራትና በሌሎችም ሥርዓቶች ዘክሯቸዋል።መንግሥት ለጠራና ላደራጀዉ ሠልፈኛ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያዉያኑን ስደተኞች «ለሞት የዳረጓቸዉ»  ያሏቸዉን ደላሎች አዉግዘዋል።ይሁንና አሶስየትድ ፕረስ የተሰኘዉ የአሜሪካ ዜና አገልግሎት እንደዘገበዉ የሐዘን መግለጫ የነበረዉ ሠልፍ መንግሥትን ወደ መቃወምና ቁጣ ተቀይሯል።ሠልፈኛዉ መንግሥትን የሚቃወሙ መፈክሮችና ዉግዘቶች ማሰማት ሲጀምር ፀጥታ አስከባሪዎች ሠልፈኛዉን ለመበተን የሐይል እርምጃ ወስደዋል።ከሠልፈኞች መካከልም በፖሊስ ላይ ድንጋይ የሚወረዉሩ ነበሩ።በግጭቱ ከሠልፈኛዉም ከፖሊስም በርካታ ሰዎች መቁሰላቸዉ ተዘግቧል።በዘገባዉ መሠረት ፖሊስ በርካታ ሰልፈኞችን  አስሯል።የቆሰሉና የታሰሩ ሰዎችን ቁጥር የሚጠቁም ዘገባ ግን እስካሁን አልደረሰንም።

dw.de.com

Posted By/ Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s