የተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የሠብዓዊ መብት ተሟጋቾች ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ይጨቁናል ሲል ሮይተር ዘገበ

አዲስ አበባ የሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራን በሌለበት ትናንት የ19 ዓመት ከመንፈቅ እስራት እንደበየነበት ሮይተርስ የዜና አገልግሎት  የመንግሥት ቃል አቀባይ ሽመልስ ከማልን ጠቅሶ ዘገበ። ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራ ከአንድ ዓመት በፊት 193 መንገደኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በመጥለፍ ስዊዘርላንድ ውስጥ ማሳረፉ ይታወሳል። በጠለፋ ሂደቱ በወቅቱ አንዳችም ሰው ጉዳት እንዳልደረሰበት፥ ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራም በገመድ ተንጠላጥሎ በመውረድ እጁን ለስዊዘርላንድ ፖሊሶች እንደሰጠ ተዘግቧል።  የ32 ዓመቱ ረዳት አብራሪ የካቲት 10 ቀን 2006 ዓም ወደ ሮም ያቀና የነበረውን የኢትዮጵያ የመንገደኞች አውሮፕላን ቦይንግ ጄትን የጠለፈው፤ ጣሊያናዊው ዋና አብራሪ ወደ መጸዳጃ ቤት ከሄዱ በኋላ እንደነበር በወቅቱ ተዘግቧል።  ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራ  ኢትዮጵያ ውስጥ ደኅንነት እንደማይሰማው በመግለጥ የጥገኝነት ጥያቄ እንዳቀረበ የስዊዘርላንድ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል ሲል የዜና አውታሩ አትቷል።  ረዳት አብራሪው በአሁኑ ወቅት በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መረጃ የለም ብሏል። የተቃዋሚ  ፖለቲከኞች እና የሠብዓዊ መብት ተሟጋቾች  ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ይጨቁናል በማለት አዲስ አበባ ውስጥ የተላለፈውን የእስራት ብይን መተቸታቸውንም ሮይተርስ አክሎ ዘግቧል።

Posted By/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s