ማርች ፰

 

ኢትዮጵያ አገራችን ለብዙ ሺህ ዘመናት ከውጭ ወራሪና ቅኝ አገዛዝ ራስዋን ነጻ አድርጋ ሉዓላዊነትዋንም አስጠብቃ የኖረች አገር ነች። በመሆንዋም በዓለም ዙሪያ በተለይም በጥቁር ህዝቦች የነጻነት ጮራና ኩራት ሆናለች፣የረቀቀ ባህልና ዕውቀት እንዲሁም የሰው ዘር ምንጭና መገኛ በመሆንዋም በዓለም የስልጣኔ እናት በመባል ታውቃለች። ሆኖም ግን ዛሬ አግራችን ያለችበት ተጨባች ሁኔታ ይህን ታሪካዊ እውነታ ከማንጸባረቅ እጅግ የራቀ ነው። ለዚህም ብሄራዊ ክብር መራቆትና ድህነት የዳረጋት  የወያኔ23 ዓመት የጎሳ አገዛዝ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው።

ከዚሁም የጥፋት ሰለባ ከሆኑት አንዱ ሴቶች ይገኙበታል  በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በመካከለኛው ምስራቅ የሰው ልጅን ስብዕና በከፍተኛ ደረጃ በሚደፍርና በሚጎዳ ዘመናዊ ባርነት ውስጥ ይገኛሉ። ድህነትንና ኢሰብአዊ አስተዳደርን ለመሸሽ ኢትዮጵያኖች ሴቶች ከአገራቸው እንዲወጡ ሲሆን በአንጻሩ በብዙሺህ የሚቆጠሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ወደ ሀገራችን በመግባት መንግስት ባዘጋጀው የሴክስ ቱሪዝም ይዝናናሉ::  አገር ውስጥ ያሉትም ሴቶች በልቶ ለማደር ወይም ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ሲሉ ወደ ማይፍልጉት ህይወት ይዳረጋሉ :: ወቅቱ  ኢትዮጵያውያን ሴቶች በተለይ ምንማድረግ ይኖርባቸዋል? ብለን እንድንጠይቅና ልዩ ጥሪ እንድናስተላልፍ ያስገድደናል።

በዚህ የህልውና ፍልሚያ ውስጥ እኛ ኢትዮጵያውያን  ሴቶች ተገቢውን ተሳትፎ ማድረግ ግዴታችን ነው። በአገራችን ታሪክ ሴቶች በብሄራዊ ጉዳይ ላይ ወሳኝና ከፍተንኛ አስተዋጽዎ ሲያደርጉ መኖራቸው የታወቀ ነው። በቅርብ ታሪካችንም ለአገራቸው ሉዓላዊነት ሆነ ለራሳችው መብት ማስከበር ግንባር ቀደም ሆነው ታግለዋል ፤መስዋእትነትንም ከፍለዋል ። ለአብነት ያህል ብንጠቅስ ከዚህ ቀድም ብርቱካን ሚደቅሳ ፣ርዮት አለሙ፣ የዞን ፱ ሴቶች ማኅሌት ፋንታሁን እና ኤዶም ካሣዬ እንዲሁም ብዙ ሴቶች አሉ ዛሬም ይህን ወሳኝ ሃላፊነት በመቀበል ለድህነትና ለባርነት የዳረጋቸውን የወያኔ የጎሳ ስርዓት ማስወገድ አማራጭ የሌለው የነጻነት መንገድ ነው ብለው ቆርጠው እራሳቸውን ወደ ወይኒ የገቡ ።

የሴቶች ጥያቄ የአገርና የሰብአዊ መብት ጥያቄ አካል ነውና ያለሀገር ህልውናም የሴትች መብት ሊጠበቅ ስለማይችል በቅድሚያ ኢትዮጵያ ሀግራችንና ህዝቧን ከአደጋ ማዳን ዋናው የኢትዮጵያውያን ሴትች ሃላፊነትና ግዴታ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s