ጋብቻ በጠለፋ (አስገድዶ መድፈር )፡ አደገኛው ተቋም በኢትዮጵያ፣

የጠለፋ ጋብቻ የሰው ልጅ ታሪክ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሲፈጸም የቆየ እጅግ በጣም ኋላቀር እና አስቀያሚ ከሆኑ ድርጊቶች መካከል አንደኛው መሆኑ የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም፡፡ በተለያዩ የሰብ ሰሀራ እና በደቡብ ኢስያ አገሮች በተለያየ መልኩ ሲተገበር ይታያል፡፡ በኢትዮጵያ በተለምዷዊው አተገባበሩ በግዳጅ በጠለፋ እንድታገባው የሚፈልገው ወጣት ጠላፊ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን በግዳጅ ለማግባት የመረጣትን ልጃገረድ ተንኮል በተቀላቀለበት መልኩ ይከተሏታል፣ እናም እንደሚታደን አውሬ አባረው ለመያዝ እና በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ወጣት ወንዶች በፈረስ ጀርባ ላይ ተቀምጠው ሴቷ ከገበያ፣ ከትምህርት ቤት ወይም ደግሞ ሌሎች ስራዎችን ልትሰራ ሄዳ ስትመለስ ወይም ስትሄድ ከበስተኋላዋ ሳታስበው እንደ ዱብ እዳ ይከቧታል፡

ስለጠለፋ ጋብቻ ያልተነገረው ታሪክ፣

አስቀያሚው የጠለፋ ጋብቻ ተቋማዊ ህይወት ለምንድን ነው በመቀጠል ላይ ያለው እና በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው? ያ በሚሊዮኖች ዶላር የሚያስወጣ ጥያቄ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የጠለፋ ጋብቻን፣ የህጻናት ሙሽራነትን እና በሌሎችም ችግሮች ላይ ግንዛቤ ወስዷል፡፡ ገዥው አካል የእንደዚያ ዓይነቱ ድርጊት መተግበር በጠቅላላ በሴቶች ላይ አዋራጅ፣ አስደንጋጭ እና ከሰብአዊነት በታች የወረደ ችግር ብቻ አይደለም የሚያስከትለው ሆኖም ግን ለአደጋው በጣም ተጋላጭ በሆኑት የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ክፍሎች እና እድሜአቸው ለአካለ መጠን ያልደረሱ የገጠር ልጃገረዶች ላይ የከፋ ይሆናል ከሚል እሳቤም ጭምር ነው፡፡ ይህ ህገወጥ ድርጊት በዓለም አቀፉ የሰብአዊነት ህግ የተወገዘ መሆኑን አሳምሮ ያውቃል፡፡ ገዥው አካል ከዚህ ጋር በሚጻረር መልኩ ግን ሴቶች የፖለቲካው የጀርባ አጥንት ናቸው በማለት ሲያውጅ ይደመጣል፡፡  እንደዚህ ያለ ኋላቀር እና እንስሳዊ ድርጊት የህብረተሰቡ ግማሽ አካል በሆኑት ሴቶች ላይ በመፈጸም ላይ ያለ አስቀያሚ ወንጀል የእርሱ የጀርባ አጥንት በሆኑት ሴቶች ላይ እየተፈጸመ እና ቀጣይ ሆኖም በመተግበር ላይ መሆኑን እያየ ያለ ገዥ አካል እንዴት እንዲህ ያለ ንግግር ሊያሰማ ይችላል? ይህንን እርስ በእርሱ የሚጣረስ አራምባ እና ቆቦ የሆነ ዝባዝንኪ ንግግር ለማድረግ የሚያስችል የሞራል ብቃትስ አለውን?

የጠለፋ ጋብቻ እና ያለእድሜ ጋብቻ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች በየዕለቱ ይካሄዳል፡፡ የእንደዚህ ያለው ልምድ መተግበር ባለፉት ጥቂት ሳምንቶች ብቻ ጠቅላላ የሆነ ማስረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ የችግሩን ስፋት እና ጥልቀት የሚያመላክቱ በጣም ጥቂት የሆኑ ተጨባጭነት ያላቸው እና ስልታዊ የሆኑ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህንን አደገኛ የሆነ ኋላቀር ባህል ለማስቀረት ወይም ደግሞ ቢያንስ ለመቀነስ የሚያስችሉ ፈጣን የፖሊሲ እርምጃዎች እና ወሳኝ የሆነ አስፈጻሚ አካል እንደሚያስፈልግ ከበቂ በላይ መረጃዎች አሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2004 የህዝብ ምክር ቤት/Population Council ትንተና እንዲህ የሚል ጥቆማ ሰጥቶ ነበር፣ “ኢትዮጵያ ጥቂት በጣም መብትን የሚጥሱ የጋብቻ ልምዶች ማለትም እንደ የጠለፋ ጋብቻ፣ ወንድም ወይም አጎት ሲሞት ወንድም በግድ ሚስቱን እንዲወርስ መደረግ የመሳሰሉት መፈጸሚያ አገር ናት፡፡“ እ.ኤ.አ በ2005 “ጎጅ ልማዳዊ ተሞክሮዎች በኢትዮጵያ/Harmful Practices in Ethiopia” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተመሳሳይ ዘገባ እንዲህ በሚል መልኩ ቀርቦ ነበር፣ “የጠለፋ ጋብቻ በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡ በአንድ የመነሻ መረጃ ለማግኘት በተደረገ ጥናት መሰረት በህብረተሰቡ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑ የልጃገረዶች ጋብቻዎች የሚፈጸሙት በጠለፋ መሆኑን ያመላክታል፡፡ የመተግበር ስፋቱ እና ጥልቀቱ ደግሞ እንደ ኦሮሚያ እና ደቡብ በመሳሰሉት ክልሎች ላይ የጠነከረ ሆኗል“ ይላል፡፡ እንደ የተባበሩት መንግስታት የ2009 ጥናት “በኢትዮጵያ የጠለፋ ጋብቻ ተደጋግሞ የመከሰት መጠኑ ከፍተኛ ሲሆን የአገሪቱ አማካይ 69 በመቶ ሲሆን በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ደግሞ 92 በመቶ” መሆኑን ያመላክታል፡፡ እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው አብይ ጉዳይ የጠለፋ ጋብቻ እና ያለእድሜ ጋብቻ ችግሮች በአንድ በተወሰነ አካባቢ ወይም ደግሞ በአንድ ክልል ብቻ የሚወሰኑ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያ በበርካታ የገጠሪቱ ማህበረሰብ አካባቢዎች የሚፈጸሙ መሆናቸው ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ግንዛቤ ለመውሰድ በጣም አስቻጋሪ ሆኖ የሚቀርበው ነገር ገዥው አካል የጠለፋ ጋብቻ ሰለባዎችን መብት ለማስከበር የሚያስችል አስፈላጊ እና በቂ ሀብት ያለው የመሆኑ እውነታነት ነው፡፡ በአስገድዶ መድፈር እና በመጽሐፍ የባለቤትነት መብት ወንጀል ላይ ግልጽ እና የማያሻሙ ህጎች አሉ፡፡ ገዥው አካል ጠላፊዎችን እና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጃገረዶችን አስገድደው የሚደፍሩ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ የሚያቀርቡ እና ህጉን ለማስፈጸም የሚያስችሉ በመላ ሀገሪቱ ተሰራጭተው የሚገኙ ከበቂ በላይ የሆኑ በርካታ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች፣ ዳኞች እና አቃብያነ ህጎች አሉት፡፡ በእርግጥ እነዚህ የሚባሉት ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች፣ አቃብያነ ህጎች እና ዳኞች በኒዮርክ እንደተደረገው ሁሉ ወደ ዝርዝር ጉዳይ ጠልቀው በመግባት የተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮችን እና አባላትን አስገድደው ለገዥው አካል በማስረከብ የተካኑ አፈ ጮሌዎች ናቸው፡፡ ሲነሽጣቸው ሽጉጥ ወይም ደግሞ AK-47 አያወጡም አይባልም፡፡ ሆኖም ግን ህጻናት የሚደፍሩትን እና የሚጠልፉትን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ለማቅረብ በአጠቃላይ ኃይልየለሽ ደካሞች ሆነው ይገኛሉ!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s