ከ1935 እስክ 1940 የጣሊያን ወረራ በኢትዮጵያና የሴት አርበኞች

የአገራችን የኢትዮጵያ ሴቶች ጦር ሚና በቂ አድርጎ ለመግለፅ በጦር ሜዳ ያልተሣተፉትንም ማንኛዉንም ሴቶች ማጠቃለል

ያስፈልጋል። ምክንያቱም አብዛኞቹ ሴቶች በኢትዮጵያ የመከላከያ ጦር ግንባር ላይ ባይሳተፉም ለጦሩ ሞራል በመስጠት (በፉከራ

በዘፈን) በአብዛኛው በአገራችን የተካሄደውን ጦርነት በድል እንዲወጣ ስንቅ ( አገልግል ) በማዘጋጀት፣ ውሀ ከወንዝ ቀድቶ በማቅረብ

በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ከጦርነት ወደ ጦርነት ለሚጓዘው የንጉስ ጦር ለድል እንዲበቃ ትልቅ ሚና በመጫወታቸው ክብር

ሊሰጣቸው ይገባል።

አንድ የታወቀ ተጓዥ እና ፀሐፊ James Bruce በአንድ ወቅት ስለነዚህ ሴቶች በጦርነት ጊዜ ያደረጉትን አስተዋፅኦ እንደገለፀው (እንዳሰመረበት )

በዚህ አለም ማንም ሴት እንደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ቀን ከለሊት ሳይለዩ፣ ሳይደክሙ፣ ሳይሰለቹ ጦሩ ወደጉዞ ይዞት የሚሄደዉን ስንቅ በማዘጋጀት

ዉሀ በእንስራ ተሸክመዉ በማጓጓዝ በማቅረብ የሚሠሩ ጠንካራ ብርቱ ሴቶች ናቸው ሲል ገልፆታል። በተጨማሪም በዕለት ዕልት ኑሮ ካልተለወጠሩ፤

መንገድ በማፅዳት፣ የተጎዱትን አርበኞች የህክምና እርዳት በመስጠት ሲሳተፉ ታይተዋል። በዚህ የስነ ልቦና ስሜትም ልእልት ፀሐይ ሀይለ ስላሴ

በጣሊያንና ኢትዮጵያ ጦርነት ጊዜ በማናቸዉም ክፍል ዉስጥ ሴቶችን በማስተባበር ለቁስለኞች ፋሻን በማድርግ ፤ልብስ በወቅቱ እንዲደርስ፤ ከጠላት

የሚወረወረውን መርዝ እንዴት አድርጎ መከላከል እንደሚቻል ስታሳይና ስታስተምር ታይቷል።በተጨማሪም ልዕልት ፀሐይ ሀይለ ስላሴ ቋንቋን

በማስተርጎም ለሀገሯ ትልቅ አስተዋፅዎ ያደረገች ልዕልት ነች ።

ስለዚህ ሁልጊዜ ማሰብና ማስታወስ ሊኖርብን የሚገባው ቀደም ብሎም ቢሆን በአድው ድል ላይ ሴቶች ምን ያህል ለሠራዊቱ በተለያየ

መንገድ ለጦር መከላከያዉ ትልቅ አስተዋፅኦ በማድረጋቸዉ ከውጭ ለመጣ ጠላት ሳይሽነፉ ለአመት ሳይሆን ለብዙ ዘመነ አመታት

ክብርና ነፃነት ሀገራችን እንዲኖራት አድርገዋል።

ሴት አርበኞች

ብዙ ሴት እርበኞች የጣሊያንን ወረራ ለማክሸፍ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል። በዚያ ወቅት በወ/ሮ ሸዋ ረገድ በኋላም በልዕልት

ተናኘወርቅ ሀይለስላሴ ተቋቁሞ የነበረ ነፃ አገልግሎት የሚሰጥ ማህበር ነበር። በዚህ ስር የነበሩ አርበኞችም በጦርነቱ ግንባር በመሠለፍ

ተዋግተዋል ከነዚህም ውስጥ ወ/ሮ ሸዋ ረገድ፣ ወ/ሮ ከበቡሽ፣ ወ/ሮ ፋንታዬ እናም ሌሎች ብዙ ስማቸዉ ያልተጠቃሱ ሴት ታጣቂ

አርበኞች ነበሩ። አብዛኛዉ የሴት አርበኞች ልዩ ያረጋቸው የነበረው የጠላት ጦር መቃረቡን ለአርበኞች በጥሩንባ ( እንቢልታ)

በመንፋት የሚያሳዉቁ ሴት አርበኞች እንደነበሩ ታሪክ ይናገራል። በተጨማሪ ከአይሮፕላን የሚወረወረዉን ፈንጂ ከምንም ሳይቆጥሩ

በከፍተኛ ቦታ በመደበቅ የጠላት ጦር በሚያልፍበት ትላልቅ የድንጋይ ናዳ በመልቀቅ፣ መንገድ በመዝጋት ይከላከሉ የነበሩ እና

መሳርያዎችን አፀዳድተው የማቅረብ አስተዋፅኦ ያረጉ የነበሩ ሴት አርበኞች እንደነበሩ መረዳት እንችላለን። እንደ ወ/ሮ ፅጌ መንገሻ ያሉ

አርበኞች የቆሰሉ ወገኖችን በህክምና ይረዱ እንደነበር ይታወቃል።

የታሪክ ፀሐፊዎቹ እንዳስቀመጡትና እንደሚገምቱት በጣም ብዙ ሴቶችም የሕይወት መስዋዕትነት ከፍለዉበታል የታሪኩ ፀሐፊ

Andrew Hilton The Ethiopian Patriots “Forgotten Voices of the Italo-Abyssinian war 1935-41 በሚለው መፅሐፉ ላይ

በሕይወት የሚገኙትን የሁለት ሴት አርበኞች ቃለ መጠይቅ ያረገዉን ለምስክርነት አቅርቤዋለሁ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s