የትግስቱ ‹‹ቡድን›› ከደህንነቶች ጋር ሆኖ በሚያደርሰው ጫና የቀድሞ የአንድነት አባላት ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ ነው ተባለ

ነገረ ኢትዮጵያ

safe_image

 

 

 

 

‹‹ለሚደርስብን አደጋ ተጠያቂው የአቶ ትግስቱ ቡድን ነው››የትግስቱ አወሉ ተወካዮች ከገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በቀድሞው የአንድነት አባላት ላይ በሚያደርጉት ጫና ምክንያት የቀድሞ የአንድነት አባላት ቀያቸውን ጥለው እየተሰዱ መሆኑን የቀድሞው አንድነት የኮምቦልቻ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ ዘሪሁን ገሰሰ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆን አትችሉም፡፡ ለትግስቱ አወሉ እውቅና ካልሰጣችሁ እናስገርፋችኋለን፡፡›› እየተባሉ ከፍተኛ ጫና እንደሚደርስባቸው የገለጸው አቶ ዘሪሁን በዚህ ጫና ምክንያት በርካታ አባላት ቀያቸውን እንዲለቁ ተገደዋል ብሏል፡፡ ‹‹ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ያለህን ግንኙነት አቁም፡፡ በዚህ ሶስት ቀን ውስጥ አገር ጥለህ ውጣ፡፡ በስልክ ከማንም ጋር እንዳታወራ፡፡ የነገርንህንም ለማንም መንገር የለብህም›› ተብያለሁ ያለው አቶ ዘሪሁን የኮምቦልቻ ነዋሪና የአቶ ትግስቱ አወሉ ተወካይ በሆነችው ወ/ር ሰብለ ይመር መሪነት ሰማያዊን የተቀላቀሉት የቀድሞው የአንድነት አባላት ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልጾአል፡፡ የትግስቱ አወሉ ተወካዮች ከደህንነቶች ጋር ሆኖው ሰማያዊን በተቀላቀሉት አባላት ላይ በከፈቱት ዘመቻ ከማህበራዊ ግንኙነታቸው መገለላቸውን፣ በስራቸው ላይ ችግር እየተፈጠረባቸው እንደሆነና በህይወታቸውም ላይ አደጋ እየተፈጠረባቸው መሆኑን የገለጹት አባላቱ ‹‹ለሚደርስብን አደጋ ተጠያቂው የአቶ ትግስቱ ቡድን ነው›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Posted By- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s