ለመኢአድ፣ ለአንድነትና ለሰማያዊ ፓርቲወች የቀረበ ጥሪ -አ ንዱዓለም ተፈራ

ይድረስ፤ ለመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (admin@keup.org)
ይድረስ፤ ለአንድነት ድርጅት (andinet@andinet.org)
ይድረስ፤ ለሰማያዊ ፓርቲ (contact@semayawiparty.org)
ከ፤ አንድ የታጋዩ ወገን ኢትዮጵያዊ
ጥር ፲ ፭ ቀን ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት

AEB

እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ፤ በሀገሬ የፖለቲካ ትግል ላይ ታች ስልበት ብዙ ዓመታትን አሳልፌያለሁ። አሁን ባለንበት የፖለቲካ ትግል ሀቅ፤ ምኅዳሩን አስፍታችሁ የያዛችሁና በትግሉ ከፍተኛውን መስዋዕትነት እየከፈላችሁ ያላችሁ እናንተ ናችሁ። የያዛችሁት ትግል ሰላማዊ መሆኑ አኩሪ ነው። መፍትሔውም በሰላማዊ ትግሉ እንደሚመጣ ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም። አሳሳቢ በሆነው የትግል ሂደታችሁ ላይ የሚከተለውን የአቤቱታ ጥሪ እንዳቀርብላችሁ፤ ኢትዮጵያዊ፣ ትውልዳዊና፣ ታሪካዊ ኃላፊነቴ አስገድዶኛል። ያንዳችሁም አባል አይደለሁም፣ አልነበርኩም። በአንድነት ስትሆኑ፤ አባል ለመሆን፤ የመጀመሪያውን ማመልከቻ ለማቅረብ ዝግጁ ነኝ።

 • ፩ኛ. ሁላችሁም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ የፖለቲካ ሥልጣኑ ምንጭና የሥልጣኑ ባለቤት ነው፤ ብላችሁ ታምናላችሁ።
 • ፪ኛ. ሁላችሁም፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና እያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ዴሞክራሲያዊ መብታቸው ተከብሮላቸው፤ በመረጡት የኢትዮጵያ ክፍል፤ ሠርተው የማደርና ሀብት የማፍራት፣ መብት አላቸው ብላችሁ ታምናላችሁ።
 • ፫ኛ. ሁላችሁም፤ አንድ ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ወይንም ኢትዮጵያዊት፤ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን፤ በሃይማኖታቸው፣ በፆታቸው፣ በትውልድ ሀረጋቸው፣ በመኖሪያ ቦታቸው፣ ወይንም በሀብታቸው ብዛት ሆነ ማነስ በማያገልና ከፋፋይ ባልሆነ የፖለቲካ ስብስብ፤ በኢትዮጵያዊ
 • ዜግነታቸውና በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ብቻ በነፃ ተደራጅተው፤ በእኩልነት በመሳተፍ፤ በሀገራችን የፖለቲካ ሂደት፤ ዓላማቸውን ማራመድ ይችላሉ ብላችሁ ታምናላችሁ።
 • ፬ኛ. ሁላችሁም፤ መሬት ለአራሹ መሆን አለበት፣ የኢትዮጵያ ዳር ደንበር መከበር አለበት፤ የኢትዮጵያ ለም መሬት፤ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርሶ እንዲጠቀምበት መሆን አለበት ትላላችሁ።
 • ፭ኛ. ሁላችሁም፤ ኢትዮጵያዊያን፤ በሀገሪቱ ውስጥ፤ ያለማንምና ያለምንም ተፅዕኖ፤ የፈለጉትን ሃይማኖት መከተልና ማክበር ይችላሉ ብላችሁ ታምናላችሁ።
 • ፮ኛ. ሁላችሁም፤ በመካከለኛው ምሥራቅ በመሰደድ፤ ነፃ ትንፋሽ ለማግኘትና ሥራ ፍላጋ እየሞቱና እየተገደሉ ያሉበትን ሀቅ በመገንዘብ፤ ይህ ጉዳይ ክፍተኛ ትኩረት እንዲሠጥበትና ባስቸኳይ መፍትሔ እንዲገኝለት ትፈልጋላችሁ።
 • ፯ኛ. ሁላችሁም፤ በዓለም ዙሪያ ተሰዶና ተበታትኖ ያለው ኢትዮጵያዊ፤ እውቀቱን፣ ሀብቱንና ጉልበቱን አሰባስቦ ወደ ሀገሩ እንዲገባና የእድገት ሚና እንዲጫወት ትፈልጋላችሁ።
 • ፰ኛ. ከላይ ለተዘረዘሩት ጉዳዮች፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብት አለመከበር፣ ድምጹ አለመሰማት፣ ተሳትፎውን በማቀብ ዋናው ተጠያቂ፤ አሁን በሀገራችን ላይ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ነው ብላችሁ ታምናላችሁ።
 • ፱ኛ. ሁላችሁም ለትግል የተነሳችሁት፤ ከላይ የተዘረዘሩት አበይት ሀገራዊ ችግሮች፤ ባጠቃላይም ሀገራችን ያለችበት የፖለቲካ ሀቅ አሳስቧችሁ ነው። ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ናችሁ።
 • ፲ኛ. በመሠረቱ ደግሞ፤ በጃችሁ ያለውን መፍትሔ፤ ሁላችሁም በአንድነት ተሰባስባችሁ ብትነሱ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሞራልና የትግል ስሜት እንደምታሳድጉ፣ ኢትዮጵያዊነትን እንደምታበለጽጉ፣ ለመታገል የሚፈልገውን ኢትዮጵያዊ ቁጥር እንደምታበዙና እንቅስቃሴው ባጭር ጊዜ ግቡን እንዲመታ እንደምታደርጉ ታውቃላችሁ።

ይህ ሀቅ በሀገራችን ላይ ሰፍኗል። እናም መሠረታዊ የሆኑት ሀገራዊ ጉዳዮች ከላይ የተዘረዘሩት ናቸው። ከነዚህ የበለጠ ክብደት የሚሠጣቸው ጉዳዮች የሉም። ስለዚህ በቁጥር አንድ የሠፈረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ሥልጣኑ ባለቤት የማድረግ ቅድሚያ ትግላችሁ፤ በአንድነት ስትሆኑና በአንድነት ስትሆኑ ብቻ ይሳካል። ከነዚህ በታች ላሉት ጉዳዮች መልስ ሠጪው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ መጀመሪያ የሥልጣኑ ባለቤት መሆን አለበት። ከዚያም ሕዝቡ የመምረጥና የመመረጥ መብቱ ሲከበርለት፤ በአንድነት በምታስኬዱት የሽግግር ወቅት፤ በሂደት በወቅቱ የሚቋቋሙትን የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ድርጅታዊ የፖለቲካ መርኀ-ግብራቸውን ሕዝቡ እየተመለከተ፤ ይመዝናቸዋል። መጀመሪያ አሁን ያለንበት ሀቅ፤ ይኼንን ዕድል የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያገኝ የምታደርጉት ትግል ነው። ታዲያ እንቅስቃሴው፤ በአንድነትና በሰላማዊ መንገድ መሆን አለበት። ስለዚህ አንድነታችሁ ወሳኝ ነው። አንድ ሳትሆኑ፤ መታገሉም ሆነ ግባችሁ መሳካቱ አጉል ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለረጅም ጊዜ ሲመኝ የነበረውን ድል ያገኛል። ይህ አይቀሬ ነው። የራሱን ዕድል በጁ ያስገባል። ይህ ውሳኔ በጃችሁ ነው። ታሪክ በዚህ መነፅር እየተመለከታችሁ ነው። የቁርጠኛ ታጋዮች መለኪያው እንዲህ ያለው የታሪክ ሀቅ ነው።
አክባሪያችሁ፤
አንዱዓለም ተፈራ

Posted By- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s