ሳዑዲ ዓረቢያ በሽብርተኝነት ጠርጥራ ካሰረቻቸው መካከል አንድ ኢትዮጵያዊ አለበት

ኢስላሚክ ስቴት ከተባለው ጽንፈኛ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ በሳዑዲ ዓረቢያ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋሉት 135 ተጠርጣሪዎች ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ግለሰብም መያዙን የሳዑዲን ፖሊስን ጠቅሰው ዘገባዎች ገለጹ፡፡

የሳዑዲ መንግሥት ባለፈው ሰኞ 135 ተጠርጣሪዎችን ማሰሩን በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ይፋ ባደረገበት ወቅት፣ ተጠርጣሪዎቹ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በማሴር ላይ እንደነበሩ ገልጿል፡፡

ከተያዙት ተጠርጣሪዎች 26 የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ናቸው፡፡ እነሱም 16 ሶሪያውያን፣ ሦስት የመናውያን፣ አንድ ግብፃዊ፣ አንድ አፍጋኒስታዊ፣ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ አንድ ባህሬናዊና አንድ ኢራቃዊ መሆናቸው ተዘርዝሯል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊውን ተጠርጣሪው ጨምሮ የሁሉም ግለሰቦች ስም ይፋ አለመደረጉን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

የሳዑዲ ዓረቢያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ 40 የሚሆኑት ተጠርጣሪዎች ግጭት ባሉባቸው የአካባቢው አገሮች ድረስ በመዘዋወር በጦርነቶች የተሳተፉና ሥልጠና የወሰዱ ናቸው፡፡

ሌሎች ደግሞ ለኢስላሚክ ስቴት የገንዘብ ድጋፍ ማድረግንና የፕሮፓጋንዳ ሥራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳዊና ሞራላዊ ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል፡፡

Source- reporter.com

Posted By- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s