“የዘረኝነት ስድብ ሲሰድቡኝ እና “ኤቦላ” ሲሉኝ እራሴን ለመከላከል ያደረኩት ነው”- የብሔራዊ ቡድናችን አጥቂ ራምኬል ሎክ ዶንግ በፖሊስ ከተወሰደ በኋላ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የመብራት ሀይሉ ተስፋ የተጣለበት አጥቂ ራምኬል ሎክ ዶንግ ትላንት በተለያዮ ድህረገፆች ስሙ ከፍርድ ቤት እና በፖሊስ ተይዞ መቅረቡ ተከትሎ በረካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።
ramkelኢትዮ-ኪክ ወደ ዋሊያዎቹ ካምፕ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በመደወል ከጋምቤላ ምርጥ ፍሬ እና የዋሊያዎቹ አጥቂ ራምኬል ጋር ያደረገውን ቆይታ እንድታነቡል ብሎም እውነታውን እንድትገነዘቡ ለማድረግ ሞክረናል።
ኢትዮኪክ:- ለቃለምልልሱ ፍቃደኛ በመሆንህ ራምኬሎ ሎክ በአንባባዎቼ ስም እናመስግናለን።
ራምኬሎ:- ኧረ ምንም ችግር የለውም!
ኢትዮኪክ:- ትላንት ምንድነው የተፈጠረው?
አሁንስ ያለኸው የት ነው?
ራምኬሎ:- ጉዳዮ ትላናንት ሳይሆን ከሳምንታት በፊት የፕሪምየር ሊጉን ጨዋታ ከመከላከያ ጋር ከማድረጋችን ከሶስት ቀን በፊት አካባቢ ኤልፖ ካምፖችን በር ላይ ቆሜ የቤተሰብ ጉዳይ እየተነጋገርኩ ሳለ የማላቃቸው ሶስት ሰዎች የዘረኝነት ስድብ እንዲሁም ‘ኤቦላ’ ብለው ሰደቡኝ ከዛ በኃላ ነው ነገሩ የተከሰተው። አሁን ያለሁት ከብሔራዊ ቡድን ጋር ሆቴል።
ኢትዮኪክ:-ጉደዮ የተፈጠረው ቀን ላይ ነው?
ራምኬሎ:- አይደለም ፤ምሽት ለሶስት እሩብ ጉዳይ አካባቢ ነው።
ኢትዮኪክ:- በዛ ሰአት ካምፕ በሩ ላይ ምን እያረክ ነበር?
ራምኬሎ:-ከአንድ ጓደኛዮ ጋር ሹፌር ነው ፤የቤተሰብ ጉዳይ እያዋራውት ነበር። ታናሽ ወንድሜ ታሞ ስለነበር ይሄ ሹፌር በዛኑ ምሽት ወደ ጋንቤላ ስለሚሄድ ለወንድሜ መታከሚያ ገንዘብ ይዞልኝ እንዲሄድ ኤልፖ በር ላይ ቀጥሬው ከእርሱ ጋር እያወራን ባለበት ሰአት ነው ይሄ ነገር የተከሰተው።
ኢትዮኪክ:- ሰዎቹ ስንት ናቸው? ታውቃቸዋለህ?
ራምኬሎ:- እነሱ ሶስት ናቸው። እንደውም አንዱ ከመሀከላቸው የፀጥታ አስከባሪ ልብስ የለበሰ ነው። ሁለቱ መጀመሪያ ‘ኤቦላ ‘ከዛም ዘረኝነት ስድብ ሲሳደቡ አጠገባቸው ያለውን የፀጥታ አስከባሪ ጓደኛቸው የተማመኑ ይመስላል። ከዛ በኃላ ሁለቱ ከእኔ ጋር ድበድብ ጀመሩ አንዱ ደግሞ አብሮኝ የነበረውን ጓደኛዮን ጋር መደባደብ ጀመረ ፣ እነሱ ሶስት ናቸው እኛ ሁለት። በዛ ላይ የፀጥታ አስከባሪ ፀጥታ ማስከበሩን ትቶ ሲሳደቡ እና ሲደባደቡ እኔም እራሴን ለመከላከል ያደረኩት የመልስ ምት ነው።
ኢትዮኪክ:- ምንድነው የደረሰው ጉዳት?
ራምኬሎ:- በድብድቡ ሰአት አንዱ ጥርሱ ወልቄዋለው መሰለኝ፣ አይኑም ሳያብጥ አይቀርም።ሲጀመር እኔ አልደረስኩባቸውም ፣ ሰውም ላይ የምደርስ አይነት ባህሪ የለኝም። እራሳቸው ተሳድበው ሲያበቁ ለመደባደብ ሲመጡ እራሴን ተከላክያለው።
ኢትዮኪክ:- ከእግር ኳስ ውጭ ራምኬሎ ቦክስ ያዘወትራለህ እንዴ?
ራምኬሎ:- [በፈገግታ] ኧሯ ቦክስ እንኳን አላዘወትርም….
ኢትዮኪክ:- ትላንት ፖሊሶች መጥው ሲወስዱህ ደንግጠህ ነበር?
ራምኬሎ:- No! ምንም የሚያስደነግጥ ነገር አልነበረውም።ጉዳዮን ሰምቼ ነበር፤ ከትላንት በስቲያ ሆቴል መጥተው ከቡድን መሪያችን ጋር ተነጋግረው እኔም እሮብ ፍርድ ቤት ቀጠሮ እንዳለኝ ስለተነከገረኝ አልደነገጥኩም። በዛ ላይ እነዚህ የከሰሱኝ ሰዎች ክለቤ በር ላይ ነው የተከሰተው ፤ እኔን መክሰስ ከፈለጉ የት እንደምጫወት ያውቃሉ። እስከዛሬ ቆይተው ብሄራዊ ቡድን ስመረጥ ጠብቀው መክሰሳቸው ሌላ ተልህኮ እንዳላቸው ያሳያል።
ኢትዮኪክ:- እጅህን በሰንሰለት ታስረህ ነበር እንዴ ወደ ህግ ቦታ ስትሄድ?
ራምኬሎ:- ኧሯ የምን ሰንሰለት ፤ እጄን ኬሴ ውስጥ ነበር [ፈገግታ]
ኢትዮኪክ:- አሁን ክሱ በምን ሁኔታ ላይ?
ራምኬሎ:- ከአልጄሪያ ጨዋታ በኃላ እንደገና የፍርድ ቤት ቀጠሮ አለኝ።
ኢትዮኪክ:- እንዴት ነው ይህ ሁኔታ የፈጠረብህ ስሜት ?
ራምኬሎ:- ኧረ ምንም ነገር አልተሰማኝም፤ እኔ ትኩረቴ ብሔራዊ ቡድኑ ነው። ከእኔ የሚፈለገውን ማደረግ ነው ለብሔራዊ ቡድናችን ማገልገል።
ኢትዮኪክ:- ዛሬ ምሽት ወደ አልጄሪያ ትጓዛላችሁ ፤ ራምኬሎ በአልጄሪያ ጨዋታ ምን ያስባል?
ራምኬሎ:- እኔ እንግድህ ብሔራዊ ቡድኑ ከተጠራው ጀምሮ ሀሳቤ አንድ ነው፤ በተቻለኝ አቅም ብሔራዊ ቡድናችን የአልጄሪያ ጨዋታ አሸንፈን መምጣት ነው የማስብው።
ኢትዮኪክ:- ስለነበረን ቆይታ ራምኬሎን ከልብ አድርገን እናመሰግናል።

ምንጭ: ኢትዮኪክ

Posted By- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s