የሚሊዮኖች ድምጽ – እስሩኝ እንጂ አንድነትን ለቅቄ አልወጣም ያሉት ሴት ታጋይ ታሰሩ !

የወላይታ ዞን ዋና ከተማ ፣ የሶዶ ነዋሪ ናቸው። ዘር ኃይማኖት ሳይጠይቅ ሁሉንም ዜጋ ለማቀፍ በሩን ክፍት ያደረገው፣ ለሁሉም ዜጎች የቆመው የአንድነት ፓርቲ አባል ናችው። ፓርቲው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ለነጻነት በሚል መርህ በበርካታ ከተሞች ህዝብባዊ እንቅስቃሴ ባደረገበት ወቅት በሶዶ ለተደረገው እንቅስቃሴ በየመንገዱ ከፍተኛ ቅስቀሳ ማድረጋቸው፣ ህዝቡ ማነጋገራቸዉና ማሳመናቸው በአገዛዙ ካድሬዎች አልተወደደላቸውም። “ለምን ወረቀት አሰራጭሽ?” በሚል ክስ ተመሰረተባቸው።

“የአንድነት ፓርቲ የምትለቂ ከሆነና አርፈሽ የምትቀመጭጪ ከሆነ ችገር አያጋጥምሽን” የሚል መደለያ ቢቀርብላቸው “ ነጻነቴን ስጡኝና ሕይወቴን ዉሰዱ” እንዳለው ፓትሪክ ሄንሪ አይነት የነጻነት ጥማትና ወኔ እንዳላቸው በማሳየት ፣ “እሰሩኝ እንጂ ከአንድነት አልወጣም” የሚል ምላሽ ሰጡ። ወ/ሮ ሃዲያ መሀመድ ይባላሉ።

 

ገዥው ፓርቲ ኢሕአደግ በሌሎች ቦታዎችም እንደሚያደርገው ፣ የግፍ ዱላውን አንስቶ፣ ምርጫው ሲቃረብ፣ በፈጠራ ክስ፣ ወ/ሮ ሃዲያ መሐመድ ለአመት እንዲታሰሩ ወስኗል። እኝህ እህታችን በአሁኑ ወቅት ለሰላም፣ ለዴሞክራሲና ለነጻነት በወህኒ ተወርዉረው ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ።

እንግዲህ የአንድነት ፓርቲ ማለት ይህ ነው። የአንድነት አባላት እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ፣ ሕይወታቸውን እየከፈሉ፣ ከስራቸው እየተባረሩ ፣ እየተደበደቡ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚታገሉ ናቸው። ገዥዊ ፓርቲ እነዚህን ወገኖቻችንን ሲያስር በንዴትና ከወገዛ ባለፍ ተግባራዊ ምላሽ ያስፍልገዋል። ለአገዝዙ አፈና እስር ተግባራዊ ምላሽ ይሆን ዘንድ ደግም፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚሊዮኖች ንቅናቄን እንዲቀላቀልና አንድነት እንዲደገፍ እንጠይቃለን።

በየክልሉ ያላችሁ ኢትዮጵያዉያን የሚያታግላችሁ ድርጅት አላችሁ፣ የአንድነት ፓርቲ። አባል በመሆን ትግሉን ተቀላቀሉ። በዉጭ ያላችሁ ደግሞ ፣ በዉጭ ብትኖሩም የሕዝቡ አካል ናችሁና አገራዊ ግዴታችሁን በመወጣት፣ በድጋፍ ድርጅቶችም ይሁን በሲቪክ ማህበራት በመደራጀት ትግሉን በሐሳብ፣ በገንዘብ ፣ በዲፕሎማሲ ደግፉ።

ለዉጥ፣ ነጻነት ጥቂቶች ስለደከሙ አይመጣም። ለዉጥ ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። ብዙዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው። እኛም የድርሻችንን ለመወጣት እንነሳ።

በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ለመከታተል የሚከተለውን የፌስ ቡክ ገጽ ላይክ ያደርጉ፡

https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj

በዉጭ አገር ያላችሁ፣ ፓርቲዉን በጽሁፍ፣ ጠቃሚና ፕሮፌሽናል አስተያየቶች በመስጠት ሆነ በማንኛዉም ገንዝበ ነክ ባልሆኑ ጉዳዮች ለመርዳት ፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል ወይንም የአንድነት ድጋፍ ድርጅት አካል ሆናችሁ መስራት ለምትፈልጉ በሚከተለው አድራሻ ኢሜል ይላኩልን።

Posted by- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s