ቅዱስ ሲኖዶስ ለኹለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ሰጠ

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ፣ ጥቅምት ፳፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የቀትር በፊት ውሎው በተመለከተው የሊቃነ ጳጳሳት ዝውውርና ምደባ አጀንዳ፣ የሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጉዳይ በመመልከት ለኹለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ሰጥቷል፡፡

His grace abune daniel, archbishop of Dire Dawa and West Harerghe

በዚኽም መሠረት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል÷ የድሬዳዋ እና ምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ መድቧቸዋል፡፡

his grace abune hizkiel

የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ አህጉረ ስብከታቸውን እንደያዙ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ ኾነው እንዲሠሩ መድቧቸዋል፡፡

ብፁዕነታቸው የተተኩት፣ የኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ኾነው ሲሠሩ በቆዩትና ተደራራቢ ሓላፊነት በነበራቸው የሶማሌ/ጅግጅጋ/ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ በኾኑት ብፁዕ አቡነ ያሬድ ምትክ ነው፡፡

ለ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በቀረበው የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት እንደተመለከተው፣ ኮሌጁ በቀን የሴሚናሪ እና የትርጓሜ ትምህርት መርሐ ግብሮቹ የሚያስተምራቸው ደቀ መዛሙርት በማታው መርሐ ግብር ከሚቀበላቸው በቁጥር በእጅጉ ያነሱ መኾናቸው በተቋሙ አስተዳደር ሊጤን የሚገባው ነው፡፡ ተቋሙ ያለፈውን ዓመት ደቀ መዛሙርት ባስመረቀበት ወቅት ከአስተዳደራዊ ነፃነት፣ ከሥርዐተ ትምህርት ዝግጅትና በመሰሏቸው ጉዳዮች ረገድ በግልጽ ያቀረባቸው ችግሮች ሳይዘነጉ የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር ማሽቆልቆል አፋጣኝ ትኩረት ሊሰጠው ያስፈልጋል፡፡

በይበልጥም አኹን በበላይ ሓላፊነት የተመደቡትና በደቀ መዝሙርነት ይኹን በመምህርነት የቤተ ጉባኤያቱ ጣዕምና አስፈላጊነት በሚገባ የሚያውቁት ብፁዕነታቸው፣ በቀን መርሐ ግብሩ ላይ የሚታየውን የቁጥር ማሽቆልቆል ከሚመለከታቸው ተባባሪ አካላት ጋራ በመነጋገር እንደሚያሻሽሉት ይታመናል፡፡

ተቋሙ ከውጭ ሀገሮች ለመጡ ደቀ መዛሙርት የነፃ ትምህርት ዕድል መስጠቱ፣ የማታውን የትምህርት መርሐ ግብር የሚከታተሉ በልዩ ልዩ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶችና ሊቃውንት ቁጥር በየጊዜው ዕድገት ማሳየቱ ሊበረታታ የሚገባው ነው፡፡

በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው፣ ባለፈው በጀት ዓመት የኮሌጁ የመምህራንና የደቀ መዛሙርት ማደርያዎች በተሟላ ኹኔታ ታድሷል፡፡ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ በከፈተው ዐጸደ ሕፃናት የአካባቢው ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ት/ቤት የሚያገኙበትን ዕድል ከመፍጠሩም በላይ ኮሌጁም ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ በ፳፻፯ ዓ.ም. የትምህርት ዘመንም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ዕውቅና ከመንግሥት አግኝቷል፡፡

Posted By- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s