የህወሓት ጠቃሚ ክፍፍል! (አምዶም ገ/ስላሴ – ከትግራይ)

የህወሓት ባለስልጣናት ከሁለት ሳምንት በፊት የትግራይ መንግስት ዓመታዊ ሪፖርት ኣድምጠው ነበር።
በወቅቱ የዞን፣ የተለያዩ ቢሮዎችና የክልሉ ኣስተዳዳሪ ሪፖርታቸው ሲያቀርቡ 100 %፣ ከእቅድ በላይ የሚሉ የቁጥር ኣገላለፅ ተጠቅሞው ለማመን የሚያዳግት ዳታ ኣቅረበው ኣልፈዋል።
በወቅቱ ህወሓትን ለ3 የከፈላት ኣንድ ሃገራዊ ጉዳይ ተነስቶ ነበር።
የመጪው ሃገራዊ ምርጫ ጉዳይ እንዴት እናድርገው? የሚል ዓብይ የውይይት ኣጀንዳ ተይዞ ውይይት ጀመሩ።
ህወሓቶች ዘውትር በኣንጃዎች የተወጠሩ ቢሆኑም የዚህ ኣጀንዳ መከፋፈል ግን ያለወትሩ ለኢትዮዽያ ፖለቲካ ጠቃሚ ነገር ይዞ መጥተዋል።
ምርጫው በተሳካ ለማከናወን ምን መስራት ይጠበቅብናል..? የሚል በተያዘ ነጥብ ህወሓት 3 ዓይነት ኣቋሞች ጎልተው ወጥተው ልዩነት ፈጥረው መግባባት ሳይደረስባቸው ቀርተዋል።
፩) “..የምርጫው ውጤት ኢህኣደግ ኣሸንፎ በሚወጣበት መንገድ ቃኝተን ለተጨማሪ 5 ዓመታት መንግስት ሁነን መቀየት ኣለብን።…” የሚል ኣንዱ ሲሆን “…የህዝቡ ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎት እንዴት እንከላከለው ለሚለው..?” ኣንጃው ሲመልስ “…ህዝብ እንደ ጎርፍ ነው በፈለግነው ኣቅጣጫ መምራት እንችላለን።..” የምርጫው መንፈስም ቀዝቃዛ በማድረግ ህዝቡ ከጅምሩ ታላቅ ተስፋ እንዳሳያድር ማድረግ ኣለብን…” የሚል ነው።
የህዝቡ ድምፅ ላለማስከበር እንደ ዋነኛ ምክንያት ወይም ስጋት ኣድርጎ የወሰደውም “…ወደ ስልጣን የሚመጣው ሃይል ሊያጠፋን ይችላል፣ እኛና ልጆቻችን የት እንገባለን…” የሚል ነው።
፪) ሁለተኛው ኣንጃ “…ምርጫው በውሱን መልኩ ዲሞክራሲያዊ መንፈስ የተላበሰ በማስመሰል የህዝቡ የለውጥ መንፈስ በሚያስተናግድ መልኩ ምህዳሩ በመክፈትና የተወሰነ መቀመጫዎች ለተቃዋሚዎች በመልቀቅ ኣሸናፊ እንደሆንን ማወጅ ኣለብን …” የሚል መከራከርያ ኣቅርቧል። የዚህ ኣቋም መነሻ ሃሳብ “….በህዝቡ የተፈጠረው የለውጥ ፍላጎት በተወሰነ መልኩ የተመለሰ ማስመሰል ይጠበቅብናል..” የሚል ሃሳብ ይዟል። የዚህ ዋነኛ መላ በስልጣን ለመቆየት ህብረተሰቡ እናዛናጋው የሚል ነው።
፫) ሶስተኛውና በጣም ጠቃሚ ሃሳብ “..እኛ የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት እያየነው ነው። ስልጣን ኣንለቅም ብንል ወደ ከፋ ኣደጋ ሊያመራን ይችላል። ለኛና ለህዝቡ የሚጠቅመው ነፃ፣ ፍትሃዊና ኣስፈላጊው ፖለቲካዊ ምህዳር በመፍቀድ ሃቀኛ ውድድር በማካሄድ ውጤቱ በፀጋ ተቀብለን በሃገራችን ኣኩሪ ታሪክ ሰርተን ማለፍ ኣለብን …” የሚል ነው። ይህ ኣንጃ “..ይህ ባናደርግ ከፍተኛ ኣደጋ ሊያጋጥመን ከመቻሉም በላይ የታሪክ ተወቃሾች ሆነን እንቀራለን…” የሚል ነው።
ሶስቱ ኣንጃዎች በዚህ ጉዳይ መግባባት ላይ ሊደርሱ ኣልቻሉም። በዚህና በሌሎች ኣጀንዳዎች ልዩነት በማየሉ መግባባት ሳይፈጠር ወደየመጡበት ተመልሰዋል።
ይሄ ሶስተኛ ኣንጃ የወሰደው ኣቋም 50ና 60 ዓመት እገዛለው የሚለው ህወሓት ውስጥ መከሰቱ ጠቃሚ ይመስለኛል
posted by Lemlem Kebede
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s