ብሄራዊ ባንክን ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ ያጭበረበረው ግለሰብ አስማረ አያሌው ተያዘ

(AddisNews)- ቁርጥራጭ ብረቶችን ወርቅ ነው ብሎ $ 95,553,413.89 ብር ከብሄራዊ ባንክ አጭበርብሮ ወስዷል ተብሎ የ25ዓመት ጽኑ እስራት እና 180ሺ ብር የተፈረደበት አቶ አስማረ አያሌው ደስታ በትላንትናው ዕለት ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ ተሰጠ::
በትላንትናው ዕለት ማታ በፌዴራል ፖሊስ እና በኢትዮጵያ የኢንተር ፖል ተወካይ ታጅቦ አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሺናል አየር ማረፊያ የደረሰው አቶ አስማረ  አያሌው ቀለል ያለ ነጭ ቲሸርት ያደረገ ሲሆን ሁለቱ እጆቹ በካቴና ቢታሰሩም ከፊቱ ግን ፈገግታ ይታይ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ የኢንተር ፖል ተወካይ የሆኑት ኮሎኔል የማነ ሰለጉዳዩ እንደተናገሩት አቶ አስማረ አያሌው ከታህሳስ 1998ዓ.ም እስከ መጋቢት 1999ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ከንግድና ኢንዱስተሪ ሚኒሰቴር ሀሰተኛ የሆነ የላኪና አሰመጪ ፍቃድ በማዘጋጀት እንዲሁም ከማዕድንና ኢኒርጂ ሚኒስቴር ሀሰተኛ የሆነ የወርቅ ጥራት ማረጋገጫ በመያዝ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውስጣቸው ቁርጥራጭ ብረታብረት የያዙ 29 የታሸጉ ሳጥኖች በማቅረብ ብሄራዊ ባንክን $ 95,553,413.89/100 ብር/ ዘጠና አምስት ሚሊየን አምስት መቶ ሃምሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ አስራ ሶስት ብር ከሰማኒያ ዘጠኝ ሳንቲም/ በውቅቱ የዶላር ምንዛሬ ደግሞ $ 9,555,341/ዘጠኝ ሚሊየን አምስት መቶ ሃምሳ አምስት ሺ ሶስት መቶ አርባ አንድ የአሜሪካን ዶላር አጭበርብሯል ብለዋል፡፡
አቶ አሰማረ ድርጊቱን መፈጸሙ ሲደረስበት በኬኒያ በኩል ከሀገር እንደወጣና ለሰባት ዓመታትም መኖሪያውን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አድርጓ እንደቆየ ታውቋል፡፡
አቶ አስማረ ፈጽሞታል በተባለው በማጭበርበር ድርጊት ክስ ተመስርቶበት ባለመቅረቡ እርሱ በሌለበት ክሱ እንደተሰማና ፍርድ ቤቱም ጥፋተኛ ብሎት የ25

ዓመት ጽኑ እስራት እና የ180ሺ ብር ቅጣት አሰተላልፎበት እንደነበር ተገልጿል፡፡
ግለሰቡ በትላንትናው እለት በቁጥጥ ስር ውሎ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፖሊስ ኮሚሽን በብሔራዊ ኢንተር ፖሎቻቸው አማካኝነት እርክብክብ ተደርጓል፡፡
የኢትዮጲያ ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የጋራ ግብረ ሀይለ ከኢንተር ፖል ጋር በመተባበር ባለፉት ጥቂት ወራት ተጠርጣሪዎችን ከተለያዩ ሀገራት የያዘ ሲሆን በቅርቡም የግንቦት 7 ጸሀፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸውን ጽጌን ከየመነ ሰነዓ እንዲሁም አቶ ሳሙኤል ዘ ሚኬኤልን ከኬንያ ናይሮቢ ይዞ ማምጣቱ ይታወሳል፡፡

Asmare Ayele Desta who fraud more than 95 Million Birr with a fake gold from Ethiopian National bank has been captured in United Arab emirates and returned to Ethiopia.

Asmare was exiled for the last 7 years and convicted to 25 years and $180 thousand Birr in absentia before he was captured by interpol and extradited to the Ethiopian police.

የኢቢሲ ዜና በግለሰቡ መያዝ ያጠናቀረውን ዘገባ ይመልከቱ

 

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s