“በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ የሚፈጠሩ ናቸው” አርቲስት መኮንን ላዕከ

 

“በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ የሚፈጠሩ ናቸው” አርቲስት መኮንን ላዕከ
“በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ
የሚፈጠሩ ናቸው” አርቲስት መኮንን ላዕከ
ጥያቄ፡- እኔ የማውቀው ሪቼ መወለድህን ነው፤ አንተ ግን ሰዎች ሲጠይቁህ የጨርቆስ ልጅ ነኝ ነው የምትለው፡፡ በትክክል
የተወለድከው የት ነው?
መኮንን፡- የሪቼ አጥቢያው ጨርቆስ አይደል…? ሰፈሩ ጨርቆስ ነው፤ ልዩ ስሙ ሪቼ ቢባልም ያው ጨርቆስ ነው፡፡ እኔ በጨርቆስ
ሲጠራ ነው ደስ የሚለኝ፡፡
ጥያቄ፡- ሰፈሬ፣ የተወለድኩበት ጨርቆስ ነው ብለህ የምትናገርበትና ይህን በመናገርህ የምትደሰትበት የተለየ ምክንያት አለህ?
መኮንን፡- የወለድኩበት፣ ክርስትና የተነሳሁበት፣አሁንም የምኖርበት ነው፡፡ አካባቢውን ውስጣ ውስጡን ሁሉ የቤቴን ያህል
አውቀዋለሁ፡፡ ጨርቆስ ውስጥ ብዙ አብሮ አደግ ወንድሞችና እህቶች አሉኝ፡፡ ስለዚህ እኔ የጨርቆስ ልጅ ነኝ፡፡ እዚያ ያለው ህይወቱ፣
አኗኗራችን፣ ጨዋታው፣ ደስታው በሙሉ ከውስጤ ጋር ተዋህዷል፡፡ ይህ ደግሞ ሁሌም የጨርቆስ ልጅ መሆኔን በኩራት እንድናገር ያደርገኛል፡፡
ጥያቄ፡- ጨርቆስን በሚመለከት ብዙ ቀልዶች ይነገራሉ፤ አንዳንዶችም ጨርቆስ አካባቢ ከሌላው የከተማችን አካባቢ የተለየ
አድርገው ሲያወሱት እንሰማለን፣ አንተንስ እንዲህ አይነት ነገሮች ገጥመውህ አያውቁም?
“በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ የሚፈጠሩ ናቸው” አርቲስት መኮንን ላዕከ
መኮንን፡- ጨርቆስን በሚመለከት ብዙ ነገሮች ሲባሉ እሰማለሁ፡፡ እንዳልከው ቀልዶችም ይቀለዳሉ፡፡ ነገር ግን የህይወት
ትክክለኛው ገፅታ ያለው እኛ ጋር ነው፡፡ በነገራችን ላይ ጨርቆስ ከድህነት ጋር ተያይዞ ሲወሳ ልንሰማ እንችላለን፡፡ እውነታው ግን
ሌላ ነው፡፡ በከተማችን ከጨርቆስ በበለጠ ድህነት የተንሰራፋባቸው አካባቢዎች ብዙ ናቸው፡፡ …በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ
ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ ውስጥ የሚፈጠሩ ናቸው፡፡ በኋላ ነው እየሰፋ የሚሄደው፡፡ ጨርቆስ ብዙ ቀልደኞችን፣ ብዙ ፀሐፊዎችን
ያፈራ የህይወትን አስኳል በኑሮህ የምትረዳበት ምርጥ አካባቢ ነው፡፡
ጥያቄ፡- ጨርቆስ ተወልደው ለትልልቅ ቁም ነገሮች የበቁና መልካም ስም ያገኙ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ አንተ እነማንን
መጥቀስ ትችላለህ?
መኮንን፡- እነ ተመስገን መላኩ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ፣ ዘነበ ወላ፣ ኢሳያስ ግዛው (ኢሳግ ስቱዲዮ)… ብዙ ናቸው፡፡ በተለያየ ሙያ
ውስጥ የተሰማሩ ከአውሮፕላን አብራሪነት ጀምሮ የጨርቆስ ልጆች ያልገቡበት የሙያ መስክ የለም፡፡ ዶክተሩ፣ መምህሩ፣ መካኒኩ፣
ኢንጂነሩ… በጥቅሉ የጨርቆስ ልጅ የሌለው ‹‹የለም›› የሚለው ቃል ውስጥ ብቻ ነው፡፡
ጥያቄ፡- እንግዲህ የተወለድከው አዲስ አበባ ያውም ጨርቆስ ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም ድረስ የንግግር ዘዬህ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ
ይወሰዳል፤ ይህ ከምን የመጣ ነው?
መኮንን፡- እኛ ሰዎች ብዙ ጊዜ በምንወዳቸው ነገሮች ተፅዕኖ ስር መውደቃችን የተለመደ ነው፡፡ እኔ እጅግ አድርጌ ባላገር
እወዳለሁ፡፡ እኛም ቤት ሆነ ጎረቤት ሰዎች ለጥየቃ ከባላገር ከመጡ አብሬያቸው ማውራት ደስ ይለኛል፡፡ ከሽማግሌዎችም ጋር
መወያየት ደስታን ይሰጠኛል፡፡ ሄድ መጣ ከሚልባቸው ሰዎችም ጋር መጫወት ደስ ይለኛል፡፡ በዚህ ጊዜ ለአነጋገራቸው ልዩ
ትኩረቱ እሰጣለሁ፡፡ የባላገሩ እና የሽማግሌዎቹ አነጋገር በእነዚያ ጊዜያት ውስጤ ገብቶ የቀረ ይመስለኛል፡፡ አሁንም ድረስ ባላገርና
ሽማግሌ ሳገኝ ከእነርሱ ጋር ማውራት ያስደስተኛል፡፡ በተለይም እኛ በተለምዶ ‹‹ቢጩ›› ከምንላቸው ጋር መጫወት ደስ
ይለኛል፡፡
ጥያቄ፡- በብዙ የኮሜዲ እና ሌሎች ገፀ ባህሪያቶችህ ሽማግሌ መስለህ ነው የምትሰራው፣ እኔ እንደውም ከሽማግሌ ውጪ
የሰራኸውን ገፀባህርይ አላስታውስም፡፡ ይህ ነገር አስበኸው የሆነ ነው ወይስ በአጋጣሚ?
መኮንን፡- ቀደም ሲል እንደገለፅኩት ከሽማግሌዎችና ከባላገር ሰዎች ጋር የማደርጋቸው ውይይቶች በእኔ አነጋገር ላይ ተፅዕኖ
አሳድሯል፡፡ በመደበኛው ህይወት ይንፀባረቃል፡፡ ከጓደኞቼ ጋር በምጫወትበት ወቅት አነጋገሩ ሳላስበው ይወጣል፣ ልማድ
ሆኖብኛል፡፡ ምናልባት ይሄ ነገር በድራማ፣ ቴአትር እና ፊልም አዘጋጆች ዘንድ መኮንን የሽማግሌን ገፀ ባህሪ ጥሩ አድርጎ
ይጫወትልኛል የሚል እሳቤ እንዲኖር አድርጎ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ግን ሌሎችን ገፀ ባህሪያትም ጥሩ አድርጌ እጫወታለሁ የሚል
እምነት ነው ያለኝ፡፡
ጥያቄ፡- እንደ ወጣት ወይም እንደ ጎልማሳ ደረቱን ነፋ ያደረገ ቆፍጣና ሰው ገፀ ባህሪን ተጫውተህ ታውቃለህ?
መኮንን፡- ከሽምግልና ውጪ እንደ ወጣት ሆኜ የሰራሁት ነበር፣ ነገር ግን ብዙም አልታይም፡፡ ከቴዲ ስቱዲዮ ጋር ነበር የሰራሁት፡፡
እሱ ቢታይ ኖሮ መኮንን ሁሉንም ሆኖ መስራት እንደሚችል ይታወቅልኝ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የሚያሰራኝ ካገኘሁ እሰራለሁ ብዬ
አምናለሁ፡፡ በሽማግሌ ገፀ ባህሪ ብቻ ተወስኜ እንድቀር ያደረገኝ የዳይሬክተሮች ምደባ ነው፡፡ እነርሱ ይህን ገፀ ባህሪ እርሱ አሳምሮ
ይጫወተዋል ብለው ካመኑ መስራት ነው ያለብኝ፡፡ ለዚህ ነው ሌላውን መስራት የማልችል እስኪመስል ድረስ በሽማግሌው ወጣ
ያለ ገፀ ባህሪ እንድሞክር ዕድል የሰጠኝ የለም፡፡ ሌላውንም ገፀ ባህሪ መስራት እንደምችል ገብቷቸው ዕድል የሰጡኝ ሳምሶን ወርቁ
እና ዳንኤል ኃ/ማርያም ብቻ ናቸው፡፡
ጥያቄ፡- በቲቪም፣ በመድረክም፣ በፊልምም ጋቢ እና ካፖርት ለብሰህ የምትታይ ከመሆኑ አንፃር ሰዎች በመንገድ ሲያገኙህ ምን
ይሉሃል?
መኮንን፡- ብዙ ሰዎች ጋቢ ለብሼ ወይም ካፖርት ደርቤ የሚያገኙኝ ስለሚመስላቸው ሸንቀጥ ብዬ ሲያገኙኝ ይደነግጣሉ፡፡ ለካ
ሽማግሌ አይደለህም ብለው የሚገረሙ አሉ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ‹‹እርስዎ›› እያሉ የሚያወሩኝ ሞልተዋል፡፡ በዕድሜ ከእኔ በላይ
የሆኑት እንደውም ወልደው ሊያደርሱኝ የሚችሉት ሳይቀሩ ‹‹እርስዎ›› እያሉ ያወሩኛል፡፡
ጥያቄ፡- የእውነት ግን… አንተ እንዲህ ሲሆን ምን ይሰማሃል?
መኮንን፡- ስለ እውነት ለመናገር ደስታ ነው የሚሰማኝ፡፡ ምን ያክል ውስጣቸው እንደገባሁ የማረጋገጥበት አጋጣሚ ስለሆነ ሁሌም
ደስተኛ ነው የምሆነው፡፡
ጥያቄ፡- ለአንድ አርቲስት የችሎታው መለኪያ ሆኖ የሚቀርበው የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ወክሎ መጫወት መቻሉ ነው፡፡ ከዚህ
አንፃር ከሽማግሌው ወጣ ብሎ ሌሎችንም የመሞካከር ዕቅዶች የሉህም?
መኮንን፡- በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህ አሁን በህዝቡ ዘንድ የምታውቅበት የሽማግሌ ምስል ይቀየራል ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች
በተመሳሳይ የሽማግሌ ገፀ ባህሪ ደጋግመው ስላዩኝ እንደ አርቲስት ሳይሆን የሆነ ቦታ እንደሚያውቋቸው ሽማግሌ ነው
የሚያስቡኝ፡፡ ለዚህም ነው ሽማግሌዎቹ ሳይቀሩ ‹‹አንቱ›› እያሉ የሚያወሩኝ፡፡ ስለዚህ ይህን ነገር ለመቀየር አንዳንድ ስራዎች
እየሰራሁ ነው፡፡ በቅርቡ ለእይታ የሚበቁ ቀየር ያሉ ገፀ ባህሪያትን እየሰራሁ ነው፡፡
ጥያቄ፡- ከዚያ በኋላ የሽማግሌው ይቀራል ማለት ነው?
መኮንን፡- አይቀርም፣ እንደውም በሌላ መልኩ ተጠናክሮ ነው የሚቀጥለው፡፡ በተለይ ከስር ያሉ ህፃናትን በጥሩ ስነ ምግባር
የመቅረፅ ሚና ያላቸው ሽማግሌ ሆነው ይመጣሉ፡፡ በዚህ ላይ የራሴን ፕሮጀክት ቀርጬ እየተንቀሳቀስኩ ነው፡፡ ልጆች
ሀገራቸውንና ባህላቸውን እዲወዱ፣ ራሳቸውን ከመኪና አደጋ እንዲጠብቁ፣ ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖራቸውና በትምህርታቸው
እንዲተጉ የሚያበረቱ ገፀ ባህሪ ሆነው ይመጣሉ፡፡
ጥያቄ፡- የኪነ ጥበብ ህይወትህ መነሻው ከየት ነው?
መኮንን፡- እኔ ሁሉ በፈጣሪ ሆነ ነው የምለው፡፡ ባይሆንማ የእኔ ሀሳብ ሌላ ነበር፡፡ ትንሽ በቀለሙም፣ ትንሽ በኳሱም ገፋ ብዬ
ነበር፡፡ ህይወትን የማሸንፈው፣ እንጀራ የምቆርሰው ከሁለቱ በአንዱ ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን የፈጣሪ ፈቃድ ሆነና ወደዚህ መጣሁ፡፡5/21/2014 “በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ የሚፈጠሩ ናቸው” አርቲስት መኮንን ላዕከ | Zehabesha
በትምህርቴ ትንሽ ደህና ነበርኩ፣ ኮሌጅም ገብቼ ኤሌክትሪሲቲ ተምሬያለሁ፡፡ በእግርኳሱም እስከ ምድር ጦር ቢ ቡድን ድረስ
ደርሼ ነበር፣ አባቴ ነው ያስተወኝ፡፡ መብራት ኃይል ገብቼ ኤሌክትሪክ ስሰራ ቆየሁና ምኑንም ሳላውቀው በቀጥታ ወደ ኪነ ጥበቡ
ዘው ብዬ ገባሁ፡፡ ኤሌክትሪሲቲ ተምሬ ተዋናይ ሆኛለሁ፡፡ ለነገሩ በተፈጥሮዬ አንድ ነገር ላይ ብቻ መቆየት ደስ አይለኝም፡፡
ኤሌክትሪኩ ሰልቸት ብሎኝ ስለነበር ኪነ ጥበብ ጥሩ የለውጥ ቤት ሆኖኛል፡፡ እዚያውም ማርኮ አስቀርቶኛል፡፡ አሁን ሲሸንጠኝ
የቤቴን የመብራት ገመድ በጥሼ ከመቀጠል ውጪ ኤሌክትሪኩን እርግፍ አድርጌ ትቼዋለሁ፡፡ ኳሱም ተረት ተረት ሆኗል፡፡
ጥያቄ፡- የኪነት ህይወትህ መነሻ ጊዜ መቼ ነው?
መኮንን፡- ጊዜው 1989 ነው፡፡ የሰፈሬ ልጅ አብሮ አደጌ ተመስገን መላኩ ከእኔ ቀድሞ ጀምሮ ስለነበር በየተገናኘንበት አጋጣሚ
ሁሉ ‹‹አንተ እኮ አርቲስት ብትሆን ያዋጣሀል›› እያለ ይወተውተኝ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ተውኔት የመፃፍ ዝንባሌው ነበረኝ፣
እተውናለሁ ብዬ ግን አስቤ አላውቅም፡፡ በወቅቱ የቴአትር አፃፃፍ ዘዴን ማወቅ እፈልግ ስለነበር መምህራን ማህበር አዳራሽ የፀጋዬ
ገ/መድህን ‹‹ሀሁ በስድስት ወር›› ሲሰራ እዚያ ወሰደኝ፡፡ እዚያው ኤሌክትሪክ መስራት ስለምችል አንዳንድ የመድረክ
መብራቶችን መስራት ጀመርኩ፡፡ አርቲስት ሳምሶን ወርቁ እዚያ ሲያገኘኝ ‹‹አንተ መስራት ትችላለህ›› አለና በማዘጋጃ ቤት
በሚታየው ‹‹የሲኦል ነፍሳት›› ቴአትር እንድሳተፍ አደረገኝ፡፡ በዚሁ ተጀመረ ማለት ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው በእግዚአብሔር
ነው፡፡
ጥያቄ፡- ትራጄዲ ገፀ ባህሪያት ይመቹሃል?
መኮንን፡- ደስ ይለኛል፡፡ ሰውን ከማሳቅና ከማስለቀስ የቱ ይሻላል ብለህ እንዳትጠይቀኝ እንጂ ትራጄዲም ሌላውም ለእኔ አንድ
ነው፡፡
ጥያቄ፡- አትጠይቀኝ ብትለኝም እጠይቅሃለሁ… ከኮሜዲ እና ከትራጄዲ የቱን ነው ይበልጥ የምትወደው?
መኮንን፡- እንደ ሰው ከጠየቅከኝ ምናልባት ኮሜዲው ሊበልጥብኝ ይችላል፡፡ እንደ አርቲስት ከጠየቅከኝ ግን ሁለቱም ለእኔ ልዩነት
የላቸውም፡፡ ስሰራ ሁለቱንም በፍቅር ነው የምሰራው፡፡ እንደውም ትራጄዲ የበለጠ ጥንቃቄ እና ተመስጥኦን ስለሚፈልግና ትንሽ
ከበድ ስለሚል ደስ ይለኛል፡፡ ሰዎች ከባድ ነገርን መወጣት ይበልጥ ደስታን ይሰጠን የለ? በነገራችን ላይ በጣም ብዙ ሰዎች
ያለቀሱበት ‹‹አያትየው›› የሚል ፊልም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት በየመንገዱ በስክሪን ይታይ የነበረ ነው፡፡ እዚያ ላይ እኔ
የምጫወታቸው ሽማግሌ ገፀ ባህሪ ብዙ ሰዎችን ያስለቅሱ ነበር፡፡ እናቴ ራሷ እስክትረሳኝና በኋላም ‹‹አፈር አባቱ ይብላ ይሄ
ሟርተኛ›› እስክትል ድረስ የተጫወትኩት ነው፡፡ በአብላጫው የተጫወትኩት ኮሜዲን ስለሆነ ሰዎች በኮሜዲያንነት ነው
የሚያውቁኝ፡፡
ጥያቄ፡- ኮሜዲያን ነኝ ብለህ ታስባለህ?
መኮንን፡- በጭራሽ አላስብም፡፡
ጥያቄ፡- ለምን?
መኮንን፡- ኮሜዲ ገፀ ባህሪያትን እጫወታለሁ እንጂ ኮሜዲያን ነኝ ብዬ አላስብም፡፡
ጥያቄ፡- የኮሜዲያን ማህበር አባል አይደለህም?
መኮንን፡- ነኝ፡፡
ጥያቄ፡- ታዲያ ኮሜዲያን የተሰባሰቡበት ማህበር ውስጥ ምን ዶለህ?
መኮንን፡- ኧረ ነገር አብርድ… ኮሜዲያን ነህ ብለው ጠሩኝ፣ ይሳቃል ኢንተርቴይመንት የተባለ ድርጅት የኮሜዲ ትርዒት
ለማሳየት ጋብዞን ሂልተንና ሸራተን ሰርተናል፡፡ የድርጅቱ ባለቤት ‹‹በማህበር ብትደራጁ መልካም ነው›› የሚል ሀሳብ ሲያመጣ
ጓደኞቼ የማህበሩ መስራች ስብሰባ ላይ ጠሩኝ፡፡ ማህበር ለማንኛውም ነገር ጥሩ ነው፡፡ ከዕቁቡም ከዕድርም ጀምሮ ያለው የጋራ
ነገር ጥሩ ስለሆነ ኮሜዲያን ነኝ ብዬ ባላስብም አባል መሆኔ ክፋት የለውም በሚል ነው አባል የሆንኩት፡፡
ጥያቄ፡- ብዙ ጓደኞችህ ‹‹መኮንን ላዕከ›› በሚለው ስም አይጠሩህም፡፡ ብዙዎቹ ‹‹አባዬ›› ነው የሚሉህ፡፡ ይህ ነገር ከክበበው
ገዳ ጋር የ‹‹ሸምሱን›› ቪሲዲ ከሰራችሁ በኋላ የተፈጠረ ነው?
መኮንን፡- በየቦታው የተለያየ ስም ነው ያለኝ፡፡ እንዳልከው እሱ ሸምሱን ሆኖ እኔ ሽማግሌውን ሆኜ በሰራነው ቪሲዲ ‹‹አባዬ››
እያለ ነው የሚጠራኝ፡፡ አጠራሩ ቀለል ያለ እና አዝናኝ ስለሆነ አፍ ላይ ቶሎ ይቀራል፡፡ ጓደኞቼ አጠራሩ ስለተመቻቸው ያው
‹‹አባዬ›› ይሉኛል፡፡ እኔን ብዙ ሰው በመኮንን የሚያውቀኝ አይመስለኝም፡፡ ድፍን የፒያሳ ሰው ‹‹አባዬ›› ነው የሚለኝ፡፡ ወደ
ተረት ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ስትወርድ ‹‹አከቤ›› ሲሉኝ ትሰማለህ፡፡ በጉራጊኛ አጎቴ ማለት ነው፡፡
ጥያቄ፡- ቡድን የመምራት ብቃትህን ብዙ ጓደኞችህ ያነሱታል፡፡ ያለህበትን ቡድን አንድ መንፈስ፣ አንድ ልብ የማድረግ ችሎታህ
ከየት የመጣ ነው?
መኮንን፡- የአንድ ሰው መገለጫው እና የሰብዕናው መጠንሰሻ ቤተሰብ ነው፡፡ ያደግኩበት አካባቢ ማህበረሰብ ለዚህ ነገር ትልቁን
ድርሻ ይወስዳል፡፡ እኔ ተወልጄ ያደግኩበት ጊቢ አስራ አራት ቤተሰብ ያለበት ነው፡፡ ለአስራ አራቱ ቤት አንድ ኩሽና (ማዕድ
ቤት)፣ አንድ ሽንት ቤት፣ አንድ ቧንቧ ነው ያለው፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ጠብ የለበትም፡፡ ሁሉም በስምምነትና በመደማመጥ ነው
ተከባብሮ የሚኖረው፡፡ በፍቅር የሆነ ነገር ሁሉ ያምራል፣ ምንም አያስቸግርም፡፡ የእኛ ሰው ደግሞ የሚያነሳሳውና የሚመራው
ይፈልጋል እንጂ ሁሌም ለመተባበር ዝግጁ ነው፡፡ በል እንዲህ አድርግ የሚለው አስተባባሪ ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡ ስለዚህ ንፁህ
ልብ ይዞ የሚገኝ ሰው ምንም ነገር ማድረግ አይከብደውም፡፡ ይህን ከተወለድኩበት አካባቢ ተምሬዋለሁ፡፡ የሁሉ ነገር ቁልፍ ንፁህ
ልብ ነው፡፡ ንፁህ ሆነህ ስትቀርበው ንፁህ ሆኖ የማይቀበልህ ማንም የለም፡፡ ቁልፉ ነገር ይሄ ነው፡፡ እንደውም አንድ ምሳሌ
ልንገርህ አንዴ አንበሳ፣ ነብርና ዝሆን ከሰው ጋር ሆነው ሰርከስ እየሰሩ በቴሌቪዥን አየሁ፡፡ እንዴት ነው ሊግባቡና ሊዋደዱ
የቻሉት ብዬ ሌሊቱን ቁጭ ብዬ አደርኩ፡፡ መልሱን ያገኘሁት ሊነጋጋ ሲል ነው፡፡
ጥያቄ፡- መልሱ ምንድነው?
መኮንን፡- ሰውዬው ነው መጀመሪያ ጫካ የሄደው፡፡ በቃ ራሱን ሰጣቸው፣ ንፁህ ልቡን ይዞ በደመነፍሱ ነው የሄደው፡፡ ልቡ5/21/2014 “በጨርቆስ ዙሪያ የሚነገሩ ቀልዶች እዚያው ጨርቆስ የሚፈጠሩ ናቸው” አርቲስት መኮንን ላዕከ
አብጦበት አልሄደም፣ የሚበላውን ሰጣቸውና በሉ፡፡ ከዚያ ደጋግሞ እንደዚያ አደረገ፡፡ ንፁህ ልብ እንዳለው ስላወቁ ወደዱት፡፡
ሲቀር ናፈቁት፡፡ ቆይቶ ሲሄድ ገና ከሩቅ አይተውት ወደ እርሱ መጡ፣ ከዚያ ‹‹ኑ ወደ ከተማ እንሂድና ሰርተን እንብላ››
አላቸው፡፡ በደመ ነፍስ ተግባብተው ያን ትርዒት አሳዩን፡፡ ንፁህ ስትሆን እንኳን ሰው አውሬም ይቀርብሃል፤ ይወድሃል፡፡
ጥያቄ፡- ሰዎችን በስራዎችህ ታስደስታለህ፣ አንተንስ ምን ያስደስትሃል?
መኮንን፡- ከጓደኞቼ ጋር ቁጭ ብለን ውይይት ስናደርግ የተለየ ደስታ አለኝ፡፡ ከዚህ ውጭ ማንበብ በጣም እወዳለሁ፡፡ ካላነበብኩ
እንቅልፍ አይመጣልኝም፡፡ ጊዜው ያለፈበት ጋዜጣም ቢሆን የማንበብ ልማድ አለኝ፡፡
ጥያቄ፡- ቦሌ አካባቢ ታይተህ አታውቅም፤ ለምንድነው?
መኮንን፡- እኔንጃ… ምክንያቱን ባላውቀውም አይመቸኝም፡፡ ፒያሳ ደስ ይለኛል፣ ጨርቆስ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ቦሌ ግን ለምን
እንደሆነ እንጃ… አይመቸኝም፡፡ ወደዚያ የምሄድበት ጉዳይ እንዲኖረኝም አልፈልግም፡፡ ምናልባት ንፅፅሩን ማሰብ ስለማልፈልግ
ሊሆን ይችላል፡፡ ግን የፈሩት ይደርሳል እንዲሉ ቦሌ አሁን ጨርቆስ ሆኗል፡፡ መሀል ቦሌ ጨርቆስ ክፍለ ከተማ እየተባለ መጠራት
ጀምሯል፡፡ የጠሉት ይወርሳል የፈሩት ይደርሳል ማለት እንግዲህ ይሄ ነው፡፡
ጥያቄ፡- በርገር ትወዳለህ? ይመችሃል?
መኮንን፡- በልቼው አውቃለሁ፡፡ እንደ በርገር ነው፤ እንደ ቤታችን በር በጣም ገር ነው፡፡ ሸጋ፣ ገራገር ነው፡፡
ጥያቄ፡- ከእከሌ ጋር በሰራሁ ብለህ ተመኝተህ አታውቅም?
መኮንን፡- ይሄን ጥያቄ ትናንት ማታም የሆነ ሰው ጠይቆኝ ነበር፡፡ እኔ ከእከሌ ጋር በሰራሁ ብዬ ተምኝቼም አስቤውም
አላውቅም፡፡ ይልቅ እስከዛሬ አብረሃቸው ከሰራኸው ማን ተመችቶሃል ካልከኝ ፋንቱ ማንዶዬ ነው፡፡ ልጅ ሆኜ በጩጬነቴ
እንዴት ተሻምተን እናየው እንደነበር አሁንም ይታወሰኛል፡፡ ‹‹የት ሄደሽ ነበር›› ሲል ሰው ሁሉ እንዴት ደስ እንደሚለው
አስታውሳለሁ፡፡ ከፋንቱ ጋር መስራቴ ልዩ ደስታን ፈጥሮብኛል፡፡ ከመስራቴም ባሻገር ያሳየኝ ባህሪ ቀለል አድርጌ በጥሩ ሁኔታ
እንድሰራ አድርጎኛል፡፡ ተተኪን እንዴት ማፍራት እንዳለብን በተግባር አስተምሮኛል፡፡ በነገራችን ላይ ጀማሪን ማስጠጋት
ዝናቸውን የሚቀንስባቸው የሚመስላቸው አሉ፡፡ ሌሎች ያላሳዩንን ፊት ፋንቱ አሳይቶኛል፡፡ ያቺ አጋጣሚ ለእኔ ልዩ ትርጉም
አላት፡፡ አሁን ባለኝ ህይወትም የፋንቱን አርአያነት ተከትዬ ነው እየተገበርኩ ያለሁት፡፡
ጥያቄ፡- በመጨረሻ ምን የምትለው ነገር አለህ?
መኮንን፡- የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡ ስለዚህ የምናደርገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር የሚወደድ እንዲሆን
በቅን ልቦና እና በንፁህ ልብ ይሁን እላለሁ፡፡ እግዚአብሔር የወደደው ነገር ከሆነ ሁሉም አልጋ በአልጋ ነው፡፡
ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ቅን እንሁን እላለሁ፡፡ ሁለተኛ ጥበብና ጠቢባንን ያላከበረ ህዝብና መንግስት አይከበርም አይከብርም ለማለት
እወዳለሁ፡፡ ባለሙያው ለሙያው ሲታገል መንግስትም ሙያውን ለማስከበር ቢጥር ለሀገር የሚጠቅም ውጤት ይገኛል፡፡
ከዚህ በተረፈ ለእኔ እዚህ መድረስ እገዛ ላደረጉትና ልረሳቸው ለማይቻለኝ ለአቶ አበበ አያሌው፣ ለመስፈን ከበደ፣ ለሳምሶን ወርቁ፣
ለክበበው ገዳ፣ ለእንዳልክ እሱባለው፣ ለያሬድ አስራት፣ ለሰላማዊት አለማየሁ፣ ለእሸቱ ታዬ፣ ለእህቴ አማከለች ላዕከ፣ ለጌታቸው
ላዕከ፣ ለአለማየሁ ላዕከ እኛን እዚህ ለማድረስ ብዙ መስዋዕትነት ለከፈሉት እናትና አባቴ እንዲሁም እስከዛሬ አብረውኝ ለሰሩት
እና ለጨርቆስ ነዋሪዎች በሙሉ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ እናንተም ታሪክ አለህና ‹‹መድረኩን እንካ ተናገር›› ስላላችሁኝ
ከልብ አመሰግናችኋለሁ፡፡

Source/www.ethiopianrivew.com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s