የአል-ሻባብ መሪ አብዲ ጎዳኔ ተገድሏል

 

አህመድ አብዲ ጎዳኔ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

የአል-ሻባብ መሪ አህመድ አብዲ ጎዳኔ መገደሉን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አረጋገጠ።

አህመድ አብዲ ጎዳኔ ባለፈው ሰኞ፤ ነኀሴ 26/2006 ዓ.ም ደቡብ ሶማልያ ውስጥ በተካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ የአይሮፕላን ጥቃት መገደል አለመገደሉን ሲያጣሩ ሰንብተዋል፡፡

ዛሬ ዐርብ፤ ነኀሴ 30/2006 ዓ.ም ማምሻው ላይ ከዋይት ኀውስ ይፋ በሆነው ዜና መሠረት ጎዳኔ በአየር ድብደባው መገደሉን የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር አረጋግጧል፡፡

አህመድ አብዲ ጎዳኔ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/አህመድ አብዲ ጎዳኔ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

የዐይን ምስክሮችም የዩናይትድ ስቴትስ ድሮን ደቡብ ሶማልያ ውስጥ በሚገኙ የአል-ሻባብ መሪዎች ላይ የሚሳይል ጥቃት ማካሄዱን ተናግረዋል።

ጎዳኔ፣ አል-ሻባብን እአአ ከ2008 ዓም አንስቶ ይመራ የነበረ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስም እጁን ይዞ ለፍርድ ላቀረበ ወይም የሚገኝበትን ለጠቆመ የሰባት ሚልየን ዶላር ወሮታ ለመክፈል ቃል ገብታ ነበር።

«የጎዳኔ መገደል በሽብርተኛነት ላይ የተገኘ ከፍተኛ ድል ነው» ያለው ዋይት ኀውስ «አፍሪቃ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የአል-ቃዒዳ ተለጣፊ አማፂያን ደግሞ ትልቅ ኪሣራ ነው» ብሏል።

ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

http://amharic.voanews.com/flashaudio.html

 

Source/voa.com

Posted By/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s