የደሞዝ ጭማሪው እንደገና ሊመረመር ነው

 

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አስቀድሞ የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራቱን ተከትሎ በመንግስት ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት

ተሰጥቶት የነበረው የደሞዝ ጭማሪ የታሰበውን ያክል አለመሆኑን ተከትሎ በሰራተኛው ዘንድ ቅሬታ ከፈጠረ በሁዋላ መንግስት  ተጨማሪ ምርመራ

ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል።

“የደሞዝ ማስተካከያ የተባለው የታለመውን የፖለቲካ ትርፍ አለማስገኘቱ ብቻ ሳይሆን በእቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማስከተሉና የኑሮ ውድነቱን በማባባሱ

በየመድረኩ ተቃውሞ እየጋበዘ ነው በሚል ሪፖርት የቀረበላቸው የመንግስት ባለስልጣናት በማሻሻያው ላይ ምርምራ እንዲካሄድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

መንግስት ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የአካባቢያቸውን ነባራዊ ሁኔታ በአስቸኳይ  አጥንተው እንዲመጡም ወስኗል።

የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ከቀረቡት አማራጮች መካከል ለዝቅተኛው ተከፋይ በአገር አቀፍ ደረጃ አንድ እርከን ጭማሪ ማድረግ ወይም ከደሞዝ ውጭ

ያሉ የሰራተኛ ጥቅማጥቅሞች ላይ እንደ  ትራንስፖርት፣ የትርፍ ሰአት ክፍያ በመሳሰሉት ላይ ጭማሪ ማድረግ  እንዲሁም በፍጆታ እቃዎች ላይ የሚታየውን ዋጋ

ንረት መቋቋም እንዲቻል ለንግድና ኢንዱስትሪ መስሪያ ቤቶች ሃላፊነት ተሰጥቶ እና ከሰራተኞች መካከል ኮሚቴ አዋቅሮ በቀጥታ ከሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት

እንዲገዙ ማበረታታት የሚሉት ይገኙበታል።

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በሃምሌ ወር መጨረሻ ጭማሪው ተግባራዊ እንደሚሆን ቢገልጹም ገንዘብ ሚኒስቴር ግን ዝርዝር ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው ጭማሪው

ከነሃሴ ወር ጀምሮ እንደሚከፈል ማስታወቁ ይታወሳል። ይሁን እንጅ ጭማሪው በያዝነው ወር ውስጥ እንዲከፈል የሚያዝ መመሪያ እስካሁን አለመተላለፉን ኢሳት

ለመረዳት ችሎአል።

መንግስት መጪውን ምርጫ አስታኮ ያደረገው የደሞዝ ጭማሪ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር አድርጓል በሚል በተለያዩ አካላት ሲተች መቆየቱ ይታወቃል።

Source-http://ethsat.com/

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s