ኢትዮጵያና ግብጽ በተባበሩት መንግስታት የጸደቀውን የውሃ ኮንቬንሽን ሳይፈርሙ ቀሩ

EthiopiaBlueNileFalls

ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችንና የከርሰ ምድር ውሃዎችን በሀገሮች መካከል እንዴት በጋራ መጠቀም እንደሚችሉ የሚደነግገው የተባበሩት መንግስታትን የውሃ ኮንቬንሽን ኢትዮጵያና ግብፅ ሳይፈርሙ መቅረታቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ. ከ1997 ጀምሮ ሀገራት እየፈረሙ እንዲያፀድቁት ክፍት ሆኖ የቆየ “Convention on the Law of the Non Navigational Uses of International Watercourses” የሚለውን ኮንቬንሽን ግብፅና ኢትዮጵያ ግን ሳይፈርሙ ቀርተዋል። ሁለቱ ሀገሮች ይህን ኮንቬንሽን ባይፈርሙም ባለፈው እ.ኤ.አ ግንቦት ወር 2014 በተባበሩት መንግስታት ፀድቆ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሆኗል።

በዚሁ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሰንደቅ ጋዜጣ የጠየቃቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ሁለቱ ሀገራት ኮንቬንሽኑን ያልፈረሙበት ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች መኖራቸውን ገልጸው ዶክተሩ ግብፅ ኮንቬንሽኑን ያልፈረመችበት ምክንያት ሲያስረዱ በኮንቬንሽኑ ስምምነት ውስጡ ከሰፈሩት ሀገረጎች መካከል፤ “ሀገራት ተሻጋሪ ወንዞችን ሲጠቀሙ ከሌሎች ተፋሰስ ሀገራት ጋር በሚዛናዊነትና በፍትሃዊነት መሆን አለበት” የሚልው አንቀፅን በማካተቱ ስምምነቱን ላለመፈረም ምክንያት ሆኗታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለምን እንዳልፈረመች ዶክተር ያዕቆብ ሲገልጹ፤ “አንድ ሀገር ተሻጋሪ ወንዝን ለመጠቀም በቅድሚያ ለተፋሰሱ ሀገራት ማሳወቅ አለበት” የሚል አንቀጽ ፈጽሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ መሆኑን አስረድተዋል።

በተባበሩት መንግስታት የሰፈረው አንቀጽ ከዚህ በፊት በቅኝ ግዛት ዘመን በግብፅና በሱዳን በ1929 እና በ1959 የተፈረመው የናይል ውሃ ስምምነት በተመሳሳይ መልኩ የላይኛው ተፋስስ ሀገሮች ማናቸውንም በናይል ዉሃ ላይ የሚያርጉትን ልማት ቀድመው ለግብፅ ማሳወቅ እንዳለባቸው እንደሚደነገግ ይታወሳል።

በሌላ መልኩ እ.ኤ.አ. በ2010 በዑጋንዳ ኢንቴቤ የተደረሰው የናይል ውሃ ስምምነት እንደሚለው የናይል ውሃን ተፋሰስ ሀገራት ጋር የናይል ውሃን በሚዛናዊነትና በፍትሃዊነት መጠቀም አለባቸው ይላል። ይህን አንቀጽ ግብፅ በጽኑ በመቃወም ስምምነቱን አለመፈረሟም የሚታወስ ነው ሲል ጋዜጣው ዘገባውን ቋጭቷል።

Source/zehabehsa.com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s