በጎደር ወረዳ አካባቢ በምትገኘው ጻኑ ግጭት ተቀሰቀሰ

ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎደሬ ወረዳ አካባቢ በምትገኘው ጻኑ ሃሙስ  ሰኔ 5 ፣ 2006 ዓም  የተነሳው ግጭት ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የወረዳው ባለስልጣናት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የሌሎች አካባቢ ተወላጆችን አካካቢውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዛቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ በረካታ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በአሁኑ ጊዜ ቴፒ ከተማ ውስጥ ሰፍረው እንደሚገኙ ታውቋል። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ ባይታወቅም አንድ ፖሊስ መገደሉን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

የፌደራል እና የክልል ፖሊሶች በአካባቢው የፓትሮል ቅኝት እያደረጉ ሲሆን፣ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ ተቋርጧል።

ግጭቱ የተነሳው የወረዳው ባለስልጣናት ጻኑ የሚባለው በደቡብ ክልል ስር የሚገኘው አካባቢ የጋምቤላ መሬት ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውንና ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ ሰዎችን በማስወጣት የአካባቢውን ተወላጆች ለማስፈር በመፈለጋቸው ነው። የጋምቤላ ክልል ሰፋፊ መሬቶች ለውጭ ባለሀብቶች እና ለህወሃት የቀድሞ ታጋዮችና በስልጣን ላይ ላሉ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በስፋት መሰጠቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

እስካሁን ድረስ ምን ያክል ሰዎች እንደተፈናቀሉ በቁጥር ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም። አካባቢው በቡና ምርቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ በርካታ የደቡብ፣ የአማራና የሌሎች ብሄረሰቦች ተወላጆች ይኖሩበታል።

በጉዳዩ ዙሪያ የጋምቤላ ክልል ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s