ኦርኪድ 42 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል ተወሰነበት

ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ የሆኑት የወ/ሮ አኪኮ ስዩም ንብረት የሆነው ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ 42 ሚሊዮን ብር ወይም 1 ሚሊዮን 700 ሺዩሮ ለ አቶ ዮናስ ካሳሁን እንዲከፍል ፍርድ ቤት መወሰኑን ሪፖርተር ዘግቧል።

የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁለቱተከራካሪወገኖችእ.ኤ.አ. ጁላይ 9 ቀን 2011 ለመጀመርያጊዜከተከበረውየደቡብሱዳንየነፃነትቀንላይበተፈጸመየሥራግንኙነትጋርበተገናኘ ነው።

አቶዮናስ ካሣሁን፣  የተለያዩ መሣሪያዎችንና ማሽኖች ከጀርመን በማምጣት ለኦርኪድ በማከራየት የደቡብ ሱዳን የነፃነት ቀን በዓል አከባበርን  ከወርኪድ ጋርአብረውለመሥራትተስማምተው ነበር። ወርኪድ ለአቶ ዮናስ ድርጅት 42 ሚሊዮን ብር ወይም 1 ሚሊዮን 700 ሺ ዩሮ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ  ለመክፈል በም/ል ስራ አስኪያጁ አቶ እንግዳ ወርቅነህ አማካኝነት የመተማመኛ ሰነድ ቢሰጥም፣ በክፍያው ወቅት ፣ ስምምነት አለመፈረሙን ክዶ ተከራክሯል። ወርኪድ ከሳሽ ሀሰተኛ ፊርማ እና ትክክለኛ ያልሆነ ማህተም  ለፍርድ ቤት ማቅረባቸውን በማመልከት ቢከራከርም ፍርድ ቤቱ የውሉ ፊርማም ሆነ ማህተሙ ትክክለኛ መሆኑን በምርመራ ማረጋገጡን በመጥቀስ ወርኪድን ጥፋተኛ በማድረግ 42 ሚሊዮን ብሩን እስከነወለዱ እንዲከፍል አዟል።

በዘገባው እንደተመለከተው ወ/ሮ አኪኮ ስዩም በኦርኪድ ላይ 99 በመቶ የሚሆን ድርሻ አላቸው። ወ/ሮ አኪኮ ኢህአዴግ እስከገባበት ቀን ድረስ ምንም ሃብት ያልበራቸውና በችግር የሚኖሩ ነበሩ። ኢህአዴግ ከገባ በሁዋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የግንባታ ድርጅት በመመስረትና ከባድ ማሽነሪዎችን በማከራየት በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉ ጥቂት ሃብታሞች ተርታ በአጭር ጊዜ ለመመደብ ችለዋል።

ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ግለገል ጊቤ አንድ ፣ ሁለትና ሶስት በሚገነባበት ጊዜ ላሰሊኒ የግንባታ እቃዎችን እና አሸዋ በማቅረብ ከፍተኛ ትርፍ አግኝቷል። በአሁኑ ጊዜም ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የማሽነሪ እቃዎችን እና አሸዋ በማቅርብ ከፍተኛ ትርፍ እያጋበሰ እንደሚገኝ ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

ከኩባንያው ጀርባ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንዳሉበትና ዋናዋ ባለሃብትም እርሳቸው መሆናቸውን ምንጮች ይጠቅሳሉ።

ኦርኪድ ፣ ቦዲይ ዋይዝ ጂም፣ ካፌ ፓኒኒ፣ ኦርኪድ ጄኔራል ኮንትራክተር፣ ኦርኪድ ትራንስፖርት፣ ኦርኪድ ትራንዚት፣ ኦርኪድ ማሽነሪ ሬንታል፣ ኤስ ኤን ኤስ ፋርም፣ ሃይላላ ቱር ኤንድ ትራቭል፣ ሜትሩሉክስ ፍላወርስ፣ ናይል ስፕሪንግ ወተር፣ ሬንቦው ጊፍት ሾፕ፣ ሪል ሳሎን፣ ስፖርት ፊልድ እና ወንደር ዊል ቢዝነስ የተባሉ ድርጀቶችን በስሩ ይዟል።

ኦርኪድ ከኢትዮጵያ አልፎ በደቡብ ሱዳን ስራዎችን መስራት የቻለው በደቡብ ሱዳን መንግስት ውስጥ ከፍተኛ የአማካሪነት ቦታዎችን በያዙት የህወሃት ጄኔራሎች አማካኝነት ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል። ከኦርኪድ በተጨማሪ መሰቦ ስሚንቶና ሌሎች በርካታ የህወሃት ድርጀቶች በደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የቢዝነስ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል።

ከፍተኛው ፍርድ ቤት በኦርኪድ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚነቱ ለወደፊቱ የሚታይ ቢሆንም፣ ኦርኪድ በውሳኔው ላይ ይግባኝ በመጠየቅ የክፍያውን ጊዜ ሊያራዝመው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። በጉዳዩ ዙሪያ የሁለቱም ድርጅቶች ባለቤቶች በኢሳት ላይ ቀርበው ለመናገር ከፈለጉ ኢሳት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s