ታፍኖ የተወሰደው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ማእከላዊ መታሰሩ ታወቀ

ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት ከትምህርት ገበታው ታፍኖ ተወስዶ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ አመት ተማሪ እና የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው መልካሙ አምባቸው በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩ ታወቀ።
በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራአስፈጻሚ አባል የሆነው ወጣት መልካሙ አምባቸው ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ ተወስዷል። ወጣት መልካሙ የአካባቢው ነዋሪ እንደመሆኑ መጠን በጎንደር ስለ ሚደረገው የድንበር ማካለል የሚያውቀውን መረጃ በመስጠቱ በመንግስ ሀይሎች ክትትል ይደረግበት እና አንዳንዴም ማስፈራሪያ ይሰነዘርበት እንደነበር ለፍኖተ ነፃነት በተደጋጋሚ ይገልጽ ነበር። ተማሪ መልካሙ ሰሞኑን ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ታፍኖ የተወሰደው ከድንበር ማካለሉ ጋር በሰጠው መረጃ እንደሆነ በቦታው የነበሩ የዓይን ምስክሮች ገልጸዋል፡፡

Posted by/Lemlem Kebede

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s