እንደበቀቀን ያሉዋትን ይዛ እምትጮህ የአለማወቅ ወይንም የዘር ወይንም የጥቅምካ እስረኛ ካድሬ

እንደበቀቀን ያሉዋትን ይዛ እምትጮህ የአለማወቅ ወይንም የዘር ወይንም የጥቅም እስረኛ…..አለቃዎችሽ ከበሮ በደለቁ ቁጥር ዜማውን እንኩዋን ሳታጣጥሚ መውረግረግ የማይደክምሽ ካድሬ ሁላ….. ግንቦት ሃያ በር ላይ ተጎልተሽ አፍሽ ለምን ተለጎመ? ዘንድሮ እጅ እጅ እሚለው ፓፓራራም ፓራራማችሁ የፈጠጠ ውሸትም ጭምር መሆኑን ልብሽ እያወቀው ስለመጣ?

ግንቦት ሃያ ሆይ!! ብንዘረዝረው መሽቶ መንጋቱ ነው…የበደልሽን ብዛት የአቅመ ቢስነትሽን ጥልቀት ስር የሰደደውና ከየትኛውም የመንግስት ተቋም የበለጠ ተቋማዊ ቅርጽ ስለያዘው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ኢምፓየርሽ (ይሄ ሲታወቅብሽ ላብ ላብ እንደሚልሽ ይታወቃል)…አንገታቸውን ቀና ስላደረጉ በመረዳታቸውም መጠን ሃገራቸውን ስለወደዱ በየቀኑ ስለሚታሰሩ ስለሚጠፉ ስለሚሞቱ ስለሚሰደዱ ንጹሃን…..

የሞት ሁሉ ሞት ኢህአዲግ ይገባናል ብሎ ማሰብ ነው…የመጨረሻው ለራስ የሚሰጥ የሞተ ግምት ይህ ነው…ሰዎቹ ስልጣን እና ሃብት የመጨረሻው ግባቸው ነው..በሰው ልጅ ስልጣኔ መስመር ውስጥ የሚያልፍ እድገት የላቸውም:: ይችን ትልቅ ሃገር..ከ80 ሚሊየን በላይ ህዝብ ያላት በተፈጥሮ ሃብትና አቀማመጥ አየር ሁኔታ ሁላ የታደለች ሃብታም ሃገር በፖለቲካ ስርአት ምክኒያት በአለም መናጢ ደሃዎች ያልተማሩ ነጻነትም የሌላቸው በተገኝው ቀዳዳም ሊያመልጡዋት የሚሹባት ሃገር ሆናለች:: ጥቂቶች በፎቅ ላይ ፎቅ ሲደርቡ አብዛኛው ፕሮፓጋንዳ ይበላል…የወንዞች ሃገር መብራትና ውሃ ላይ ታጣጥራለች…. ስልክና ኢንተርኔት ህዝቡን በመፍራት ብቻ ኔትዎርክ ይቆለፍበታል::

ዛሬ ደርባባ እናቶች ሃፍረታቸውን አሽቀንጥረው ለልመና ይወጣሉ የተማሩ ኮብልስቶን ያነጥፋሉ ያልተማሩ አቃጣሪ ካድሬዎች ቀበሌና የመንግስት መስሪያቤት ውስጥ ወሬ በመፍለጥ እንጀራ ይጋግራሉ:: ዛሬም ከ6.5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ምጽዋት ይጠብቅባታል:: በየአመቱ በዘርፈብዙ የድህነት መለኪያ መስፈርት መሰረት ከአለም ሁለተኛዋ መናጢ ደሃ ትባላለች…ትናንት ከተፈጠረችው ኤርትራና መንግስት አልባ ሆና ከኖረችው ሶማሊያ ጋር በፉክክር ትነጻጸራለች…ከ2000- 2009 ብቻ 11.7 ቢልየን የአሜሪካን ዶላር በኢ-ህጋዊ መንገድ ወጥቶአል:: ሰዎች ባያውቁ ይመረጣል ሲያውቁ ሲረዱ የመሪዎቹን ባዶነት የሃገሪቱን ሰው አልባነት ሲረዱ ይጠይቃሉ ሲጠይቁ ይታሰራሉ…

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s