በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም አማላጅነት እንዲያቆሙ ተደረገ

 

በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላለፉት ቀናት ሲያካሂዱ የነበረውን የረሀብ አድማ ዛሬ በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም አማላጅነት እንዲያቆሙ ተደረገ፡፡ ፕ/ር ለእስረኞቹ፣ ስርዓቱ የያዙትን መንገድ እንደማይረዳው እና እንዲህ አይነት ትግል የሚሰራው መጀመሪያ የሰብዓዊነት ትርጉም እና ክብር የሚገባው ስርዓት ሲኖር እንደሆነ አስረድተው እስር ቤት ውስጥ ሆነው ከሚታገሉ ወጥተው እንዲታገሉ በመምከር ቢያንስ አሁን ምግብ እንዲወስዱ አሳምነው ይዘውት የመጡትን ቸኮሌቶች እንዲመገቡ አድርገዋል፡፡
6 የሰማያዊ ፓርቲ አመራር እና አባላት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ያለምንም ክስ በእስር እየማቀቁ ሲሆን በርካቶችም ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸል ፡፡ በተለይ ወጣት ዮናስ ከድር ፈተና እንዳይፈተን ከመከልከሉም በላይ በደረሰበት ከፍትኛ ድብደባ መንቀሳቀስ እንደማይችል መዘገቡ ይታወሳል፡፡
(በፎቶው ላይ የምታዩት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ በረሀብ አድማው ምክንያት ታሞ ከሆስፒታል መልስ በፖሊስ ጣቢያው በር ላይ እጁ በካቴና እንደታሰረ ፕ/ር መስፍን ሲያነጋግሩት)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s