ሲፒጄ» ኢትዮጵያ ፕሬስን በድጋሚ በማዳከም ጋዜጠኞችን አስራለች ሲል መግለጫ አወጣ

የጋዜጠኞች ደኅንነት ጥበቃ ኮሚቴ በእንግሊዘኛ ምኅፃሩ «ሲፒጄ» ኢትዮጵያ ፕሬስን በድጋሚ በማዳከም ጋዜጠኞችን አስራለች ሲል መግለጫ አወጣ። ኮሚቴው ባለፈው ሳምንት የታሰሩትን ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማሪዎች በተመለከተ ባወጣው መግለጫ እስራቱ በሀገሪቱ ሀሳብን በነፃ የመግለፅ እንቅስቃሴ ላይ  የከፋው ማዳከም ነው ብሏል። የ«ሲፒጄ» የምሥራቅ አፍሪቃ ተወካይ ቶም ሮዴስ «በቅርቡ በተፈፀመው እስራት  የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሀሳብን በነፃ የመግለፅ ሠላማዊ እንቅስቃሴን ወደ ወንጀል እየቀየሩ ነው» ብለዋል። የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፤  እስረኞቹ ጋዜጠኞች እንዳልሆኑ፣ እስራታቸውም ከጋዜጠኝነት ጋ ግንኙነት እንደሌለው፣ ሆኖም ከከባድ የወንጀል እንቅስቃሴ ጋ እንደሚገናኝ ተናግረዋል ሲልም ኮሚቴው ጠቅሷል። «ሲፒጄ» በበኩሉ «የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ውዥንብር ውስጥ ከመግባትና አንባገነን ከመሆን ታቅበው የሰላ ሂሳዊ ፅሁፍና ሕዝባዊ ውይይት እንዲጎለብት ይፍቀዱ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን» ብሎዋል። መግለጫው ሲጠቃለልም ለእስር የተዳረጉት ጋዜጠኞች  ቤተሰብና ጠበቃ እንዳያያቸው ተከልክለው  በማዕከላዊ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ እስር ቤት ይገኛሉ ሲል ጠቅሷል። «ሂውማን ራይትስ ዎች» የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት እንዲሁም «አምነስቲ ኢንተርናሽናል» የተባለው የመብት ተሟጋች፤ የድረገፅ ጸሐፍቱና ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወቃል።  

Source/www.dw.de,com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

One Response to ሲፒጄ» ኢትዮጵያ ፕሬስን በድጋሚ በማዳከም ጋዜጠኞችን አስራለች ሲል መግለጫ አወጣ

  1. Wonderful post! We are linking to this particularly great post on our website.
    Keep up the great writing.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s