የእንግሊዝ መንግሥት የፀረ ሽብርተኝነትና የበጎ አድራጎት ሕጎች ተቃዋሚዎችን ፀጥ አሰኝተዋል አለ

የእንግሊዝ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዝንና ዲሞክራሲን በተመለከተ ባለፈው ሐሙስ ባወጣው እ.ኤ.አ. የ2013 ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከምርጫ 97 በኋላ ሥራ ላይ ያዋላቸው የፀረ ሽብርተኝነት፣ የበጎ አድራጎትና ሌሎች ሕጎች ተቃዋሚዎችን ለመቆጣጠርና ፀጥ ለማሰኘት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው በማለት ክፉኛ ተቸ፡፡

ሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ከምርጫ 97 በኋላ የወጡትን ሕጎች በመጠቀም ተቃዋሚዎች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና፣ የእንግሊዝ መንግሥትን ክፉኛ እንደሚያሳስበው ገልጿል፡፡ የፀረ ሽብርተኝነትና የበጎ አድራጎት ሕጎችም በሪፖርቱ ከፍተኛ አጽንኦት ተሰጥቷቸው ተዳሰዋል፡፡

የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ከወጣ በኋላ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችና ሌሎች ለእስር መዳረጋቸውን ሪፖርቱ ገልጾ፣ የበጎ አድራጎት ሕጉም በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል በማለት የሕጎቹን አፋኝነት አትቷል፡፡

የሪፖርቱ ክፍል 11 በዋነኝነት በአገሮች የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ እንደማሳያነትም የ28 አገሮችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ተንትኗል፡፡ ከእነዚህም አገሮች መካከል ተጠቃሽ በሆነችው ኢትዮጵያ የእስረኞች አያያዝን በተመለከተ ባቀረበው ትንተና የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የእስረኞ መንገላታት መኖሩን አስረድቷል፡፡

ይህ የእስር ቤቶችን ሁኔታ የሚዘረዝረው ሪፖርት የተጠናቀረው 170 የሚሆኑ እስር ቤቶችን በመጐብኘት መሆኑን፣ ምርመራው የተካሄደውም ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት በተለምዶ ‹‹ማዕከላዊ›› የተሰኘው እስር ቤት በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በእስረኞች አያያዝ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ወቀሳ ይሰነዘርበታል በማለት ሪፖርቱ አትቶ፣ በእስር ቤቱ ውስጥ ግርፋትና መንገላታት መኖሩን ጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ‹‹ልዩ ፖሊስ›› የተባለው ኃይልም እያደረሰ ያለው የመብት ጥሰት ሪፖርቱ ዋነኛ ትኩረት ካደረገባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡

ምንም እንኳን የተጠናከረ የፀጥታ ቁጥጥር መኖሩ ለክልሉ ያመጣቸው የመሠረታዊ አገልግሎትና የመሠረተ ልማት ዕድገትና አንዳንድ ጠቀሜታዎች መኖሩን ሪፖርቱ አስረድቶ፣ ‹‹በልዩ ፖሊስ›› ኃይል አባላት በክልሉ ተፈጸሙ ያላቸው ግርፋት፣ ማሰቃየትና ግድያ መኖራቸውን በመግለጽ ክፉኛ ይኮንናል፡፡

በዚህ የተነሳም የ‹‹ልዩ ፖሊስ›› አገልግሎቱ እንዲሻሻል የእንግሊዝ መንግሥትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና ሳደሩ ፡፡

Source/Reporter.com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

One Response to የእንግሊዝ መንግሥት የፀረ ሽብርተኝነትና የበጎ አድራጎት ሕጎች ተቃዋሚዎችን ፀጥ አሰኝተዋል አለ

  1. Dulcie says:

    I have special neurosis universal reports that will help
    you earn good income consistently. Direct mailing neurosis universal is a great supplement to your
    marketing messages at regular intervals. You can usually specify to the company handling your direct mailing confidently and
    expediently.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s