”ትንቢተኛው” ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር ምን ይሰራል ?

”ትንቢተኛው” ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር ምን ይሰራል ?

ሰሞኑን ጠቀላያችን አንዴም ሲደንሱ አንዴም ”ሲቀደሱ” በየሚዲያው እያየናቸው ነው። እሰይ እንዲህ ነው እንጂ የኔ አንበሳ በዬ ላደንቃቸው እፈልጋለሁ። ይሄንን ፎቶ ያገኘሁት ከፌስ ቡክ ተሰውረው በትዊተር የመሽጉ ጎበዞች ዝንድ ነው። ከዛም በማስፍንጠሪያ ተስፈንጥሬ ”ትንቢተኛው” ድረ ገጽ ወስጥ ብገባ በኢትዮጰያ ቆይታው አባ ዱላ ግእና ሃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ለሌሎችም ባለስለጣኖች ቡራኬ እንደሰጠ ይናገራል።

እገረ መንገዱን ባለስልጣኖቻችን እስር እና ግርፉን እንዲተዉ ስልጣንም ከእግዜር እንጂ ከጠብ ምንጃ ዘንድ እንዳልሆነ ነግሮልን ከሆነ ደህና ነው!

ዝም ብሎ የወደፊት እጣ ፈንታቸውን ብቻ ነግሯቸው ከተመለሰ ግን ዝም ብሎ ነው የለፋው፤ የባለስልጣኖቻችንን እጣ ፈንታ እኛም እንነግራቸው ነበር። (አያያዙን አይቶ… ) እንዲል የሀገሬ ሰው ማለት ነው።

ማላዊውን ትንቢተኛ እንደኔ ለማታውቁት ከዩቲዩብ ላይ ያገኝሁት አንድ ስራውን በድረ ገጻችን ውስጥ እንደሚገተለው አሰቀመጠዋለሁ፤

የምር ግን ለጠቀላያችን እና እና ለአባዱላችን ምን ተንብዮላቸው ይሆን…  ?

በቪዲዮው ውስጥ አንዷን ደረባባ (ማሊያዊት ሳትሆን አትቀረም) ከአንድ እውቅ እና ትልቅ የኢትዮጵያ ባለስጣን ጋር የፍቅር ቁርኝት መስርታ እንደነበር ህዝብ ፊት ሲነግራት አይቼ ያ ባለስልጣን ማን ይሆን… ብዬ ለማወቅ ጓጓቴንም አልደብቅዎትም፤ ማን ያውቃል ባላየነው ቪዲዮ ደግሞ ባልስጣኖቻችንን ከማላዊት ኮረዳ ጋር ፍቅር የመሰረትክ ውጣ… በሎ አስለፍልፏቸው ይሆናል።

ጭማሪ፤
ባለስለጣኖቻችን ግን እግዚአበሄር ኢትዮጵያን ”በበረከቱ ይጎብኛት” ሲባል እንደዛ እነዳልሳቁ ዛሬ ምን ታያቸው… ወይስ የኢትዮጵያ እግዜር እና ”የትንቢተኛው” እግዜር ይለላያያሉ… ?

Source/www.abetokichaw.com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s