ጠላፊዎቻችን ጠለፋ በዛባቸውሳ…! (ትምህረተ ስላቅ እንዴት ነበረች?)

ከአቤ ቶክቻው

ጠላፊዎቻችን ጠለፋ በዛባቸውሳ…! (ትምህረተ ስላቅ እንዴት ነበረች?)

c16ea4ed65c7d5880e1b493a5f5042ba_Lያው እንደምናውቀው ወይም እንደማናውቀው በኢትዮጵያ የሰዎችን የስልክ፣ የኢሜል እና ሌሎች ግንኙነቶች መንግስት መጥለፍ ከፈለገ ባሻው ግዜ እንዲያደርገው ለራሱ በህግ ፈቅዷል። ባለፈው ጊዜ አንድነት ፓርቲ ”የጸረ ሽብር ህጉ” ተሰርዞ አግባብ ባለው ፍትሃዊ ህግ ይተካ ሲል አንዱም ይሄንንም ጨምሮ መቃወሙ ነበር።

ታድያ ሰሞኑን ለራሳቸው በህግ የጠላፊነት መብት የሰጡት ባለስልጣኖቻችን በስብሰባ ላይ ሲሰድቡን ተጠለፉ፣ አንድ በሉ፤ የአውሮፕላን ጠለፋውን እዚህ ውስጥ እናስገባው እንዴ… ካላቸሁ ሁለት በሉ… አሁን ደግሞ ሶስተኛ የሴቶች ወጣቶች እና ህፃናት (ባጠቃላይ የሰዎች ጉዳይ) ሚኒሰቴር የሆኑት ወይዘሮ ዘነቡ ግብረ ሰዶምን የሚደግፉ ሃሳቦችን በትዊተራቸው ትዊት ካደረጉ በኋላ ጠለፋ ተከናውኖብኛል… አሉ…!

እውነት ተጠልፈው ነው… የሚለውን እርሱ ጠላፊው እና ተጠላፊው ይወቁት…

ይህንን አስመልክቶ ግን አቶ ሽመልስ ከማል ሲናገሩ፤   ‹‹የሚኒስትሯን አካውንት ጠልፈው በመግባት የእሳቸውንና የመንግሥትን አቋም የማይገልጽ መልዕክት ያስተላለፉት ግለሰቦች ጉዳይ ከተጣራ በኋላ፣ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ሽሜ እግረ መንገድዎን ጠላፌው መንግስትዎ ላይም መቼ ርምጃ እንደሚወሰድ ይነገሩና!

የሆነስ ሆነና ጠላፊዎቻችን ጠላፊያቸው በዛሳ… የመጨረሻው ዘመን መጣባቸው እንዴ!?

ለማንኛውም ውይዘሮዋ ትዊት ያደረጉትን በድረ ገፃችን አስቀምጠነዋል እስቲ ፊደል አጣጣላቸውን የምታውቁት ሰዎች አጣሩልን… (እዝችጋ ሳቅ አለ)

 

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s