ሰበር ዜና፤ ወያኔ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገው የስለላ ወንጀል ስለተጋለጠ አሜሪካ ውስጥ ክስ ተመሠረተበት

ሰበር ዜና
ወያኔ በውጭ በሚገኙ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ላይ በሚያደርገው የስለላ ወንጀል ስለተጋለጠ አሜሪካ ውስጥ ክስ ተመሠረተበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለ22 ዓመታት የግድያ፣ የማሰቃየት፣ የማፈንና ሌሎችም ዘግናኝ ወንጀሎችን ሲፈጽም የኖረው ወያኔ “ተሸሽጎ የሚኖር ነገር የለም” እንደሚባለው አሜሪካ ውስጥ በሚገኘው የኢሳት ጋዜጠኞች ላይ ያካሂድ የነበረው የስለላ መረብ በመበጣጠሱና እጅ ከፍንጅ በመያዙ በዛሬው ዕለት ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውስጥ ክስ እንደተመሠረተበት ታላቁ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስታውቋል። ክሱን የመሠረተው አሜሪካ ውስጥ ላለፉት 22 ዓመታት የኖረው ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ  ግለሰብ ሲሆን የወያኔ አገዛዝ የአሜሪካን ህግ በመጣስ የስለላ መረቦችን በግልኮምፒውሩ ላይ በማስጠመድ ግለሰቡ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ሲከታተል እንደነበር ተመልክቷል። ይህ የተመሠረተው ክስ የቅርብ የአሜሪካን መንግስት ወዳጅና ተመጽዋች የሆነው የወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚዎችን፣ጋዜጠኞችንና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችን፣ የማፈን ታሪክ ያለው ከመሆኑም በላይ የተራቀቁ የድረገጽ መሳሪያዎችን በመጠቀም ጠላቶቼ የሚላቸውን ሲሰልል መገኘቱን ምልክት የሚሰጥ መሆኑ በጋዜጣው ውስጥ ተጠቁሟል።ክሱን ያቀረበው “Electronic Frontier Foundation” በመባል የሚጠራው የሰብዓዊ መብት
ተከራካሪ ድርጅት ጠበቃ የሆኑት ሚ/ር ኔት ካርዶዞ እንደገለጹት “የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተለይም ከተቃዋሚ
ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚላቸውን እንደሚሰልል መረጋገጡን አስታውቀዋል።

የወያኔ ወኪሎች ስለቀረበባቸው ክስ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው የሰጡት መልስ የተለመደ ክህደታቸውንና ቅጥፈታቸውን ነው። የኮምፒውተር ተመራማሪዎችእንዳረጋገጡትየወያኔ አገዛዝ የአፈናና የስለላ ወንጀሎችን ከሚፈጽሙ አገሮች ተርታ ውስጥ ይገኛል።ከአራት ወራት በፊት ነጻ የሆነው የጥናትና ምርምር ተቋም የወያኔ አገዛዝ “ፊን እስፓይ”በመባል የሚጠራ የጆሮጠቢ መረብ እንደሚጠቀም መረጃዎች መገኘታቸውን የሚያሳይ ዝርዝር ዘገባ አቅርበው ነበር። ቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኝውዓለም-አቀፍ ጉዳዮችትምህርት ቤት የወያኔ አገዛዝ የስለላውን መረብ ብቸኛ ተጠቃሚ መሆኑን አርጋግጠዋል። ይህ ሪፖርት ከወጣና ዜናው ከፍተኛ ሽፋን ከተሰጠው ከ5 ቀናቶች በኋላ የወያኔ አገዛዝ መጋለጡን በማወቅ ያካሂድ የነበረውን የስለላ መረብ ማቋረጡ ታውቋል። ሆኖም የወያኔ የስለላ መረብ ባላሟሎች እንዳይያዙ መረጃዎችን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርቦሽ ቢያደርጉም ሙሉ በሙሉ አሻራቸውንለማጥፋት ሳይችሉ በመቅረታቸው እጅ ከፍንጅ ሊያሲዝቸው የሚችል መረጃ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ወያኔ እንግሊዝ አገር ውስጥም በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞች ላይ የሚያደርገው ስለላ ስለተደረሰበት ተጨማሪም ክስ ተመስርቶበታል።ከዚህለማጠቃለል የሚቻለው ወያኔ የአሜሪካን ህግ በመጣስ አማሪካ መሬት ላይ የፈጸመው ወንጀል ከአሜሪካ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት በእጅጉ እንደሚያበላሽበት አይጠረጠርም። የዚህ ወንጀል መፈጸም መጋለጥና ክስ መመስረት ለወያኔ አገዛዝ ድጋፍ የሚሰጡ የአሜሪካን ባለሥልጣኖችንም ጭምር በወያኔ ድፍረትና ጥጋብ በአገራቸው ምድር ላይ ወንጀልመፈጸሙ በእጅጉ እንደሚያበሳጫቸውና እንደሚያስቆጫቸው እንዲሁም “ያሳደኩት ውሻ ነከሰኝ” እንደሚያስብላቸው ይገመታል። በአጠቃላይ ወያኔ ይህንን የስለላ ወንጀልሲፈጽም እጅ ከፍንጅ መያዙ እንደ መንግስት ሳይሆን ወንበዴነቱን፣ሌብነቱን፣ማጅራት መቺነቱንና ኪስ አውላቂነቱን በዓለም-አቀፍ ደረጃ ያሳየና እርቃኑን ያስቀረው መሆኑን ለመገመት  አያዳግትም። ከዚህም በተጨማሪ ወያኔ ከደደቢት ዋሻ ውንብድናውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በርካታ ደረቅ ወንጀሎችን ለምሳሌም ባንኮችን፣ ትምህርትቤቶችን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፣ ቤተክርስቲያኖችን፣ የግለሰቦችን መኖሪያ ቤቶችን፣ ሱቆችንና ሌሎች የኢትዮጵያውያንን ንብረቶችን መዝረፍ፣ ሀኪም ቤት የተኙ በሽተኞችንከአልጋቸው አውርዶ መሬት ላይ በመጣል አልጋቸውን መዝረፍ፤ ሌሎችንም ወንጀሎች ሲፈጽም መኖሩና ብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን ወርቅ በምትሃት ወደ ቦንዳነት የለወጠ በርካታ ኩንታል ቡና ወደ አቧራነት የቀየረ መሆኑ አይዘነጋም።

Source/www.ethiopianrevew.com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s