በኢትዮጵያ ሰሚ ያጣ ጩኻት፥ የኦሞ ሸለቆ ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ ተፈናቀለ ተባለ

ኢትዮጵያ ለስኳር ፋብሪካ ልማት ግብዓት በሚል የኦሞ ሸለቆ ነዋሪዎችን በኃይል በማፈናቀል ሠፋፊ የመሬት ይዞታዎችን  ለሸንኮራ አገዳ ተክል እየመነጠረች ነው ሲል Human Rights Watch የተሰኘው የሠብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ገለፀ። የሠብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ይፋ እንዳወጣው ዘገባ ከሆነ፣ በመንግስት የልማት እንቅስቃሴ ሰበብ በኦሞ ሸለቆ አካባቢ በኢትዮጵያና በኬንያ በጥቅሉ  ወደ 500,000 የሚጠጋ ነባር ነዋሪ ተፈናቅሏል።  በኦሞ ሸለቆ ውስጥ ሰፋፊ መንግስታዊ የስኳር ተክል ፕሮጀክቶች እንደሚገኙና ተጨማሪ በርካታ አዳዲስ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ እንደሆነም የሠብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ አስታውቋል። አያይዞም መንግሥት ሕብረተሰቡ የተሻለ የትምህርትና የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ይረዳዋል በሚል በሚያከናውነው የ«መንደር ምሥረታ» በተሰኘው እንቅስቃሴ ከቀዬያቸው በግዳጅ ጭምር የሚፈናቀሉት በአብዛኛው አርብቶ አደሮች ናቸው ብሏል። የHuman Rights Watch የአፍሪቃ ክፍል ኃላፊ ሌስሊ ሌፍኮው፦

«አብዛኞቹም እዚያ መሬታቸዉ ሲመነጠር አይተዋል፤ ወደሌላ ስፍራ አንዳንዴም ወደ መንደሮች ተወስደዉ በግዳጅ እንዲሰፍሩ ተደርገዋል። እናም የኑሯቸዉ ሁኔታ እጅግ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነዉ።»

በሌሎች አካባቢዎች እንደሚታየው ሁሉ በኦሞ ሸለቆ ነዋሪዎችን ከቀዬያቸው የማስነሳቱ ሂደት በፍቃደኝነት አለመሆኑንም ሌስሊ ሌፍኮው  አክለው ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ኢኮኖሚውን በዋናነትም የግብርና ዘርፉን ዘመናዊ በማድረግ ሀገሪቱን እጎአ በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ እንድትሰለፍ አደርጋለሁ ማለቱን የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

Source/www.dw.de.com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s