በመምህር ግርማ ወንድሙ ላይ የተወሰደው እርምጃ እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው::በአዛውንት የሃይማኖት መምህራን ላይ የሚደረገውን ወከባ እንቃወማለን::በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል!!!

Minilik Salsawi –

የአዲስ አበባ ፖሊስ መምህር ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ሥር አዋለ። ሲል የገዢው መደብ አፈቀላጤ የሆነው ራዲዮ ፋና መምህር ግርማ የተባሉትን የሃይማኖት አባት በማጣጣል ዘገባ አስተላልፏል::ለመሆኑ መምህር ግርማ በሕወሓት ከሚመራው እና በሙስና ከተዘፈቀው የተዋህዶ መሪዎች ቡድን በላይ ሙስና እና ማጭበርበር ፈጽመው ነው በቁጥጥር ስር የሚውሉት???በመጀመሪያ በቁጥጥር ስር መዋል ያለባቸው በሕወሓት እየተመሩ የተዋህዶን ጓዳ ደጁን ሙልጭ አድርገው የዘረፉ የመዘበሩ መሆን አለበት::ይህ ደሞ ጳጳሳቱ በየስብሰባቸው የሚናገሩት የሚወያዩበት የወሰኑት የአደባባይ ሃቅ ነው::መምህር ግርማ እኔ የሃይማኖቱ አባል ባልሆንም በሚዛናዊ መስመር ከሄድን በቁጥጥር ስር ሊውሉ አይደለም በሙሉ አይን መታየት የለባቸውም::

ጉዳዩን ከመምህር ግርማ የውጪ ጉዞ ጋር አስታኮ ከፖለቲካው ጋር በማቆራኘት ለማስደንገጥ ከታሰበ አመት ቢሞላውም መምህር ግርማ ላይ ምንም አይነት ወንጀል ይሁን በውጪ ከሚኖሩ የለውጥ ሃይሎች ጋር ግንኙነት እንዳሌላቸው የደህንነት ቢሮ ማስረጃዎች ያሳያሉ:: መምህር ግርማ ወደ ውጪ በበረሩ ሰአት ሁሉ ከጀርባቸው ይከተሏቸው የነበሩት ሰላዮች በመምህር ግርማ ላይ ያቀረቡት ሪፖርት መምህሩ በፖለቲካ አይደለም ከፖለቲከኞች ጋር ምም ግንኙነት እንዳሌላቸው አረጋግጧል::ታድያ መምህሩን ማዋከብ መወንጀል ለምን አስፈለገ? በማህበራዊ ድረገጽ የጥላቻ ዘመቻ መክፈት ለምን አስፈለገ???

ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ የለም ይህ የታወቀ ጉዳይ ነው::ገና ከመያዛቸው “አጥማቂ ነኝ ባዩ” አጭበርባሪው ” ወዘተ የሚሉ የመወንጀያ ስም ማጥፋቶች በመምህር ግርማ ላይ መደረጉ የሞተውን የስጋዊ/አለማዊ ሕግ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊውም ሕግ ደርቦ መግደላቸውን ሊዘነጉት አይገባም ::በፍርድ ቤት ያልተወሰነበት ሰው ድንገት ከአይሮፕላን አውርዶ በሰንሰለት አስሮ እያዋከቡ መወንጀል ነገን ከተጠያቂነት አያስተርፍም:ይህ ባዶ ጭንቅላት ፈሪ አገዛዝ መውደቂያውን እያፋጠነ ነው::በመምህር ግርማ ወንድሙ ላይ የተወሰደው እርምጃ እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው::በአዛውንት የሃይማኖት መምህራን ላይ የሚደረገውን ወከባ እንቃወማለን::በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል!!!

 

 

Minilik Salsawi's photo.

Posted By-Lemlem Kebede

 

Advertisements